ቀጣይ የሙያ ግንባታ
In order for health workers to provide quality care and meet their communities’ changing health care needs, they must become lifelong learners dedicated to updating their professional knowledge, skil
In order for health workers to provide quality care and meet their communities’ changing health care needs, they must become lifelong learners dedicated to updating their professional knowledge, skil
ለሕክምና ወደ ውጪ ሀገር የሚሄድ ኢትዮጵያዊ ጤንነቱ፤ደህንነቱ እና ክብሩ ተጠብቆ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል የሕግ ማእቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በሀገር አቀፍ ደረጃ የውጪ ሀገር የሕክምና ቅብብሎሽን ወጥ የሆነ አተገባበር ስርዓት በመዘርጋት አላስፈላጊ የታካሚን እንግልት መቀነስ፣ ለህክምናው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በተሟላ መልኩ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት፣አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 አንቀጽ አንቀፅ 58(2) መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡
በእረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ -----/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተሽከርካሪ አደጋ የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ስልጣን እና በአንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው አስቸኳይ የህክምና እገልግሎት እንዲያገኝ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀም እረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
በእረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 05/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡
የተሸከርካሪ አደጋ ተጎጅዎች የሶስተኛ ወገን መድን አዋጅ 799/2005 ዓ.ም በጸደቀው መሰረት በሁሉም ጤና ተቋማት እስከ ሁለት ሺህ ብር አገልግሎት በነፃ እንዲያገኙ ተደንግጓል፡፡ ይህንም አዋጅ መሰረት በማድረግ በተሻሻለው በደንብ ቁጥር 554/2016 የድንገተኛ ህክምና ወጪ እስከ አስራ አምስት ሺህ ብር እንዲሻሻል የተደረገ ሲሆን ለዚህም እረቂቅ መመሪያ በመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ተዘጋጅቷል፡፡
በእረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እስከ ጥር 05/2017 ዓ.ም ድረስ አስተያየቱን ታች ባለው ቅፅ በመሙላት ወይንም በሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገለጸዋል።
በመድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን ዙሪያ ለመምከር በተዘጋጀው የከፍተኛ ሃላፊዎች መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመዱ ተህዋስያን የሚያስከትሉትን ተጽእኖ ለመቀነስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራና ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች፣ አስፋላጊውን ክትትል ማድረግና የምርምር ስራዎችን እንደምታጠናክር ገልጸዋል። ይህ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስተሯ አስምረውበታል።
አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማት አበርክቷል።
እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ላስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA77) ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን ተቀብለዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ያስታወሱት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭርሃም ንጉሴ፤ የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጤና ዘርፍ ሁለቱ ሃገራት በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ዋነኛው መሆኑን አምባሳደሩ ያስረዱ ሲሆን፤ በተለይም በልብ ህክምና፣ የጨቅላ እጻናት ጽኑ ህሙማን እና የእናቶች ጤና እንዲሁም የአካል ድጋፍ እና መልሶ ማገገም ዘርፎች ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ ከ1000 ለሚበልጡ ይልብ ህሙማን ህክምና መስጠት የቻለው ሴቭ ቻይልድስ ሃርት ልኡካን ቡድን በጥቁር አንበሳ የልብ ማእከል የልብ ህሙማን ልየታ፣ የባለሙያዎች ስልጠና፣ እና የልብ ቀዶ ህክምና ማድረጉ በውይይቱ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የጽኑ ህሙማን ህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የባለሙያዎች ስልጠና መሰጡትንም ልኡካኑ አስታውቀዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር ዉይይት ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ተደረሽ ለማድረግ፣ ጤናን እና ስነ ምግብን፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን እና የኤስዲጂ ኢላማዎች ከግብ እንዲደርሱ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር ጠንካራ አጋርነት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
የጌትስ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት ቢል ጌትስ ጋር በተደረገው ውይይት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ሚኒስትሯ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
እ.ኤ.አ. ከ 2018 በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል ጌትስ ከጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋርም ዉይይት አድርገዋል።
በብራዛቪል ኮንጎ እየተካሄደ ያለዉ 74ኛው የአፍሪካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ቀጥሏል።
በመድረኩ በአፍሪካ በተለያዩ ግዜያት ወረርሽኞችና ሌሎች ድንገተኛ የጤና አደጋዎች እየተከሰቱ የማህበረሰቡ ጤና ስጋት መሆናቸዉ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል።
ኢቦላ፣ ኮቪድ 19 እና ሌሎች ወረርሽኞች በአፍርካ ቀጠና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በማስታወስ አሁን ላይ ኤም ፖክስ (Mpox) የደቀነዉ የጤና አደጋ በተለይ ለአፍሪካ አሳሳቢ መሆኑ ተንስተዋል።
በመደረኩ ላይ በመገኘት ሀሳባቸዉን ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ (Mpox) የተጠረጠረም ሆነ የተያዘ ሰዉ አለመኖሩን ጠቅሰዉ በሽታዉ እንዳይከሰት፣ ከተከሰተም ለመቆጣጠር የሚያስችል ሰፊ የቅደመ መከላከልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል።
በታንዛኒያ አቅራቢነት የተወዳደሩት ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ ኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በለዉ 74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ አባል አገራት በሰጡት ድምጽ አብላጫ በማግኘት ቀጣዩ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን ተመርጠዋል።
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዶ/ር ፉስቲን ኤንጅልበርት ንዲጉሊሌ የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት እንዲመሩ በመሰየማቸዉ እንኳን ደስ ያሎት ብለዋቸዋል።