የቀዶ ህክምና፣ የድንገተኛና ጽኑ ህክምና አገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።
የጤና ሚኒስቴር ከደብረብርሀን ዩንቨርሲቲ፣ ከስማይል ትሬን (Smile Train) እና ከኬፕ ታውን ዩንቨርሲቲና ጋር በመቀናጀት ለ3 ቀናት በአዲስ አበባ ሲያካሂድ የነበረውን የዓለም የቀዶ ህክምና፣ የድገተኛና ፅኑ ህሙማን ህክምና አገልግሎት የአመራር ክህሎት ዓውደ ርዕይ ተጠናቋል፡፡
በጥናታዊ ዓውደ ርዕዩ የማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ እንደተናገሩት አውደ ርዕዩ በዓለም አቀፍ የቀዶ ሕክምናና የድንገተኛና ጸኑ ህክምና ላይ ትኩረት አድርጎ መወያየቱ የሚደገፍና ትክክለኛው ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው እንደ ሃገር የአገልግሎቱን ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋፋት የጤና ሚኒስቴር በ5 ዓመቱ እስራቴጂክ ዕቅድ አካቶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡