በአፍሪካ የሚከሰቱ ወረርሽኞችንና ድንገተኛ የጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር “ለአፍሪካ ችግር የአፍሪካ መፍትሄ” በሚል መርህ አገራት በጋራ መስራት ይጠበቅብናል። የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር፣ ዶ/ር መቅደስ ዳባ
በብራዛቪል ኮንጎ እየተካሄደ ያለዉ 74ኛው የአፍሪካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ቀጥሏል።
በመድረኩ በአፍሪካ በተለያዩ ግዜያት ወረርሽኞችና ሌሎች ድንገተኛ የጤና አደጋዎች እየተከሰቱ የማህበረሰቡ ጤና ስጋት መሆናቸዉ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል።
ኢቦላ፣ ኮቪድ 19 እና ሌሎች ወረርሽኞች በአፍርካ ቀጠና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በማስታወስ አሁን ላይ ኤም ፖክስ (Mpox) የደቀነዉ የጤና አደጋ በተለይ ለአፍሪካ አሳሳቢ መሆኑ ተንስተዋል።
በመደረኩ ላይ በመገኘት ሀሳባቸዉን ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ (Mpox) የተጠረጠረም ሆነ የተያዘ ሰዉ አለመኖሩን ጠቅሰዉ በሽታዉ እንዳይከሰት፣ ከተከሰተም ለመቆጣጠር የሚያስችል ሰፊ የቅደመ መከላከልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።