Articles

ኢትዮጵያ የአደጋ ጊዜ የሕክምና ቡድን (EMT) አቅሟን በማጠናከር ዓለም አቀፍ የጤና አጋርነቷን እያሰፋች ነው

ACHIEVE Africa

የጤና ሚኒስቴር ከጀርመን ኤምባሲ፣ ከሮበርት ኮች ኢንስቲትዩት እና ከዓለም የጤና ድርጅት (WHO) ጋር የአደጋ ጊዜ የሕክምና ቡድኖች ተነሳሽነት እና አጋርነት በተመለከተ  የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የጀርመን አምባሳደር ብርጊት ኦሪ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የአደጋ ጊዜ የሕክምና ቡድኖች  ዓለም አቀፍ ስብሰባ እንደምታስተናግድ አስታውቀዋል፣ ይህም አገሪቱ የተጠናከረ የአደጋ ጊዜ ምላሽ አቅም መገንባቷን እና የማርበርግ ቫይረስን ጨምሮ የቅርብ ጊዜ ወረርሽኞችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መከላከል መቻሏን ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ የሚኒስትሮች የጎንዮሽ ስብሰባ በኢትዮጵያ በህጻናት ጤና እና በምግብ ዋስትና ረገድ የተመዘገቡ ስኬቶችን ማሳየት ችላለች

12

በአፍሪካ የህፃናት ጤና እና ስርዓተ-ምግብ ላይ ያተኮረው መድረክ የአፍሪካ ህብረት የስርዓተ-ምግብ ሻምፒዮን የሆኑት የሌሶቶ ግርማዊ ንጉሥ ሌቲ ሳልሳዊ፣ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ ኢትዮጵያ የሌማት ቱሩፋት እና  የአረንጓዴ ሌጋሲ አስርት ዓመታት ተነሳሽነቶችን በተሳካ ሁኔታ በመተግበር ጉልህ ውጤቶችን ማስመዝገባን ተናግረዋል።

እንደ አቶ አደም ገለጻ፣ ፕሮግራሞቹ በመላ አገሪቱ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እናቶችንና ህጻናትን የተመጣጣኝ ምግብ አቅርቦትን በማሻሻልና የመቋቋም አቅምን በማጠናከር ተጠቃሚ አድረገዋል።

መንግስት የተመጣጠነ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የምግብ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠው፣ ቀጣይነት ያለው ጥረት የወደፊት ትውልድ ደህንነትን ለመጠበቅ እንደሚያስችል አፅንዖት ሰጥተዋል።

የአፍሪካን የክትባት እና የሕክምና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው ግዙፉ "ACHIEVE Africa" የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ከ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በይፋ ተመሠርቷል 

Dr Mekdes Daba

​በኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ2040 የክትባት ፍላጎትን 60 በመቶ በአህጉር ውስጥ ለማሟላት ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች መሆኑን የገለጹ ሲሆን መንግስት የመድኃኒት ግዥ ስርዓቱን በአገር ውስጥ ለሚመረቱ ምርቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ በማሻሻሉ፣ በዘርፉ የአገር ውስጥ ፍላጎትን ሽፋን ከ8 በመቶ ወደ 42 በመቶ ማደጉን ጠቁመው በቀጣይ አምስት ዓመታት ወደ 60 በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
\
​ኢትዮጵያን የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) ለማድረግ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ የሀገሪቱ የክትባት የማምረት ጉዞ አሁን ላይ "ይሳካል ወይ?" የሚለው ጥያቄ ቀርቶ "እንዴት እና በምን ፍጥነት?" ወደሚለው ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውሰዋል።