Articles

በኢትዮጵያ በስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች በተሰራዉ ስራ ተምሳሌት የሚሆን ዉጤት ተገኝቷል - የሌሴቶ ንጉስ ግርማዊ ሌቲ ሳልሳዊ

nutrition

የሌሴቶ ንጉስ ግርማዊ ሌቲ ሳልሳዊ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በአዲስ አበባ በሚገኘው ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የህፃናት እንክብካቤ እና የስርዓተ-ምግብ ክፍልን ጎብኝተዋል፣ በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ የእናቶችን እና የህፃናትን ጤና ለማሻሻል ያላትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ግርማዊ ንጉስ ሌቲ “ውጤታማ የስርዓተ-ምግብ እርምጃ ህይወትን ያድናሉ” በማለት አፅንኦት ሰጥተው፤ በኢትዮጵያ  በስርዓተ-ምግብ ማሻሻያ እርምጃዎች በተሰራዉ ስራ ተምሳሌት የሚሆን ዉጤት ተገኝቷል ብለዋል። ስርዓተ-ምግብ በሽታን በመከላከል እና የህፃናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚናም ገልጸዋል። 

ንጉሱ እንዳሉት ኢትዮጵያ እናቶችን እና ህፃናትን ለመጠበቅ የምታደርገውን ጠንካራ ጥረት በገዛ ዓይናቸው ለማየት መቻላቸውን ተናግረው፤ አገሪቱ ስርዓተ-ምግብን ከጤና አጠባበቅ አደረጃጀቷ ጋር በማዋሃድ ዘላቂ የጤና ውጤቶችን ለማሳካት የሚያስመሰግን እና ስትራቴጂካዊ አቀራረብ መከተሏን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን በመቆጣጠር ረገድ ስኬታማ ሆናለች 

Dr Mekdes Daba

ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን በመቆጣጠር ያደረገችው ስኬታማ ጥረት በጠንካራ አመራር፣ ፈጣን ምላሽ እና በተቀናጀ እርምጃ ትልቅ የህብረተሰብ ጤና ስኬትን ማስመዝገቧን የኤፌዴሪ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ታገሰ ጫፎ ገልፀው፤ ስኬቱ የጤና ፖሊሲ፣ የጤና ባለሙያዎች፣ እና ባለድርሻ አካላት የጋራ የመተባበር እና የመደመር ውጤት ነው ብለዋል።
 
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ  በሃገራችን የጤና ታሪክ ትልቅ የስኬት አሻራ የጣለ ተሞክሮ መሆኑን ገልፀው፤ ማህበረሰቡን በማስተባበር ፈጣን ምላሽ በመስጠት ቫይረሱ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በአዲስ ቴክኖሎጂ ህክምና የሚሰጥ የመጀመሪያው የስትሮክ ህክምና ማእከል በዛሬው እለት ተመርቆ ተከፍቷል።

stroke treatment center

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሠ በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንዳሉት የጤናው ዘርፍ በርካታ መሻሻሎች እያሣየ ያለ ቢሆንም ገና ብዙ ወደ ፊት መሄድ ይጠበቅበታል ብለዋል። የአክሶል ስትሮክ እና ስፓይን ማእከል መከፈቱ እንደ ሀገር የእስትሮክ ህክምናን አንድ ምእራፍ ወደ ፊት የሚወስድ መሆኑን ጠቅሰው ማእከሉ  ለዚህ ምረቃ በመድረሱ ያላቸውን አድንናቆት ገልጸዋል። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ እና የተለየ አገልግሎት ይዞ የመጣ ማእከል በአገሪቱ መከፈት መቻሉ ለጤናው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።


ላለፋት አመታት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና በዚህ ሳቢያ የሚመጣ ሞት እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ዶክተር ሊያ ይህን ችግር ለመቅረፍ የጤና ሚኒስቴር ከመከላከል ስራው ጎን ለጎን የስፔሻሊቲ ህክምና አገልገግሎት ማስፋፋት ስራ የሚያሰራ የአስር አመት ፍኖተ ካርታ  ተዘጋጅቶ እየተተገበረ መሆኑን አስረድተዋል።