Articles

79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ይገኛል

WHA79


በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ እየተካሄደ በለዉ 79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።


በጉባኤዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ይፋ የሆነዉ የህብረተሰብ ጤና ዳሰሳ ጥናት ግኝት መሰረት ኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞትን በመቀነስ ረገድ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቧን በመግለጽ በቀጣይም አለም አቀፍ የጤና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ለመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲፈጠር በትጋት እንደሚሰራ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል። 

ኢትዮጵያ እንደ ዓለም ጤና ጉባኤ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮችን በመጠቀም የጤና ዲፕሎማሲን በማጠናከር ላይ ትገኛለች - የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ 

WHA79

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በ79 ነኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ገብቷል።


ዶ/ር መቅደስ ለልዑካን ቡድኑ ኦሪየንቴሽን በሰጡት መድረክ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በተለይም እንደ የዓለም ጤና ጉባኤ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮችን በመጠቀም የጤና ዲፕሎማሲን በማጠናከር ላይ ትገኛለች ብለዋል። 


ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት አባል ሀገር እንደመሆኗ በጉባኤዉ በሚወሰኑ ዉሳኔዎችና ቀጣይ ስራዎች የራሷን ድርሻ እንደምትወጣ ዶ/ር መቅደስ ተናግረዋል።


ወቅታዊ የኢቦላና ሀንታ ቫይረስ ሁኔታን ጨምሮ ሌሎች የዓለማችን ስጋት የሆኑ ወርሽኞችን መከላከልና መቆጣጠር በዋናነት በጉባኤዉ ቀርበዉ ዉይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጣቸዉን ኃላፊነት አስመልክቶ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ዉጤታማ  ውይይት አድርገዋል 

AI

በውይይታቸዉም በተለያዩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፤ በተለይም በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጣቸዉን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረዋል።


የፈጠራ ሥራዎች ለአፍሪካ ዕድገት ምንጊዜም ወሳኝ መሰረት ናቸዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል።