ችላ የተባሉ የትሮፒካል በሽታዎች (NTDs) ፕሮግራም

NTD

ችላ የተባሉ የትሮፒካል በሽታዎች (NTDs) በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ላይ ከባድ ህመም የሚያስከትሉ የጥገኛ ህዋስና የባክቴሪያ በሽታዎች ስብስብ ናቸው። የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለስምንት በሽታዎች የህዝብ ጤና ላይ ባላቸው ተፅእኖ መሰረት ቅድሚያ ሰጥቷል። እነዚህም ዓይን ማዝ(ትራኮማ) ፣ በአፈር የሚተላለፉ ሄልሚንትስ (STH) ፣ ሺስቶማሲያሲስ፣ ሊምፋቲክ ፊላሪያሲስ (LF) ፣ ኦንኮሴርካ(ኦንኮ) ፣ ድራንኩላ/ጊኒዎርም (GWD) ፣ ቁንጭር(ሌሽማንያሲስ) እና ፖዶኮኒኦሲስ ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት(WHO) ስኬቢስን እንደ አንድ NTD በቅርቡ እውቅና ሰቶታል።

ሚና እና ኃላፊነት

 • በ NTD መከላከል ፣ ቁጥጥር፣ የማስወገድ እና የማጥፋት ጥረቶች ውስጥ አመራር መስጠት እንዲሁም ከልማት አጋሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በአጋርነት መሰማራት።
 • የክልል መንግስትን ባለቤትነት፣ ተሟጋችነት ፣ ቅንጅት እና አጋርነትን ማጠናከር፣
 • የ NTD ጣልቃ ገብነትን እና የጤና ስርዓት ማጠናከሪያን ተደራሽነት ማሳደግ ፣
 • ለብሔራዊ የNTD ፕሮግራሞች ውጤት ተኮር ዕቅድን፣ የሀብት ማሰባሰብን እና የፋይናንስ ዘላቂነትን ማሻሻል፣
 • በNTD ውስጥ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የፕሮግራም ተሟጋችነት፣ በተለይም በሀገር፣ በክልላዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች ሀብቶችን ማሰባሰብ
 • ብሔራዊ ግቦችን ለማሳካት የ NTD ፕሮግራም ክትትል እና የግምገማ ሂደትን የሚያሻሽሉ ፕሮግራሞች መንደፍ። የክትትል እና የአሠራር ምርምርን ማሳደግ እና ማጠንከር።

ግብ

የተቀመጠውን ብሔራዊ መርሃ ግብር ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ የፈጠራ ፣ ከፍተኛ ጥራት እና ወጪ ቆጣቢ አቀራረቦችን በመጠቀም የNTDዎችን ሸክም መቀነስ::

 

የፕሮግራም ወሳኝ ምዕራፍ እና ተነሳሽነት

 

1. በ 2025 በትራኮማ የሚፈጠር ዓይነ ስውርነትን ማስወገድ

 

 • ከ5 እስከ 9 ዓመት በሆኑ ሕፃናት ውስጥ አክቲቭ ትራኮማን ከ 5% በታች መቀንስ
 • ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት እና ከዚያ በላይ በሆኑ (ወይም ከጠቅላላው ሕዝብ መካከል <0.1%) ውስጥ የትራኮማቶይስ ትሪኪያሲስ (TT) ብዛት ወደ <1% መቀነስ

 

2. ሺስቶማያሲስን በ 2025 የህዝብ ጤና ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ድረስ ማስወገድ።

 

 • በካቶ-ካትዝ (KK) የምርመራ ዘዴ የሺስቶሚያሲስ በሽታ ብዛትን ወደ <2% መቀነስ ወይም በሁሉም የአተገባበር ክፍሎች ውስጥ ከ1% ያነሰ የከባድ ኢንፌክሽን ብዛትን ማስጠበቅ።

 

3. በአፈር የሚተላለፉ ሄልሚንቶችን በ 2025 የህዝብ ጤና ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ማስወገድ

 

 • በካቶ-ካትዝ (KK) የምርመራ ዘዴ የሺስቶሚያሲስ በሽታ ብዛትን ወደ <2% መቀነስ ወይም በሁሉም የአተገባበር ክፍሎች ውስጥ ከ1% ያነሰ የከባድ ኢንፌክሽን ብዛትን ማስጠበቅ።

4. በ 2025 ሊምፋቲክ ፊላሪያሲስን ማስወገድ

 

 • ከ 6 እስከ 7 ዓመት ባሉ ሕፃናት ውስጥ የሊምፋቲክ ፊላሪያሲስን ማይክሮፊላሬሚያ <1 ወይም አንቲጂኔሚያ ከ 2% በታች መቀነስ

 

5. ኦንኮሰርኪያሲስን በ 2025 ማስወገድ

 

 • ለኦንኮሰርኪያሲስ የተጋለጡ ሕፃናት (<10 ዓመታት) ውስጥ የኢንፌክሽኑን ብዛት ወደ 0.1% መቀነስ

 

6. ጊኒ ዎርም (ድራኩኑኩላሲስ)

 

 • የሰው እና የእንስሳት ጊኒ ዎርም በሽታ ስርጭትን አቋርጦ በ 2024 ወደ ዜሮ ማምጣት

7. የውስጥ አካላት ሌሽማንያሲስ/VL  በሽታን መከላከል እና መቆጣጠር

 

 • በVL ምክንያት የሚፈጠር የሞት መጠንን ከ 3% በታች መቀነስ

 

ስልታዊ ጣልቃ ገብነቶች

 

 • የመከላከያ ኬሞቴራፒ / የጅምላ መድሃኒት አስተዳደር
 • የተጠናከረ የበሽታ-አስተዳደር
 • የቬክተር ቁጥጥር
 • ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ መሰረታዊ ንፅህና እና የንፅህና አጠባበቅ አገልግሎቶች እና ትምህርት
 • የዞኖቲክ በሽታ ቁጥጥር