Articles

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ባለዉ የዓለም ጤና ጉባኤ የጎንዮሽ መድረኮች በተለያዩ የጤና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዉይይት ተካሂዷል

#WHA79

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ባለዉ የዓለም ጤና ጉባኤ የጎንዮሽ መድረኮች የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በተገኙበት በተለያዩ ጤና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዉይይት ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ፣ ጊኒ፣ ኔፓል፣ እና አጋር አካላት ጋር በትብብር ባዘጋጀችዉ የጎንዮሽ መድረክ የድንገተኛ፣ ቀዶጥገና ህክምና አገልግሎትን በተመለከተ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ባጋሩት ገለጻ ታካሚን ማእክል ያደረገ የድንገተኛ ቀዶጥገና ህክምና አገልግሎት ማጠናከርና ተደራሽ ማድረግ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋንና የጤና ዋስትናን ለማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና ባርቤዶስ በጤናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

#WHA79

ኢትዮጵያና ባርቤዶስ በካሪኮም የትብብር ማእቀፍ በቀጠናው ባሉ ሀገራት መካከል በትብብር ለመስራት በሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት እና ማእቀፍ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።


የዚሁ ትብብር መስክ አካል የሆነ በጄኒቫ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም የጤና ጉባኤ #WHA79 ጎን ለጎን በጤናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በሁለቱ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች የተፈረመ ሲሆን ስምምነቱ በዋናነት በሀገራቱ መካከል የአቅም ግንባታ እና ክህሎት ሽግግር፤ የባለሙያዎች ትብብርና በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳም ይታመናል።

79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ይገኛል

WHA79


በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ እየተካሄደ በለዉ 79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።


በጉባኤዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ይፋ የሆነዉ የህብረተሰብ ጤና ዳሰሳ ጥናት ግኝት መሰረት ኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞትን በመቀነስ ረገድ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቧን በመግለጽ በቀጣይም አለም አቀፍ የጤና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ለመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲፈጠር በትጋት እንደሚሰራ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል።