የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ረዳት ጸሐፊ ዶ/ር ማማዲ ይላ ጋር በመንግስት ለመንግስት  የሚሰሩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

  • Time to read less than 1 minute
Dr Mekdes Daba

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ መንግስታት በጤናዉ ዘርፍ ዘርፈብዙ የትብብር ስራዎችን ለረጅም ግዜ በጋራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዉ በተለይም  የዲጂታል ጤና አገልግሎትን በማስፋፋት፣ የወባ ወረርሽኝን በመከላከል፣ የእናቶችና ህጻናትን ጤና በመጠበቅ እንዲሁም የቲቢ እና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትን በመግታት ረገድ ዉጤቶች መገኘቱን ተናግረዋል።


​በቀጣይም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አገልግሎትን  በማጎልበት ጠንካራ የጤና ስርዓትን ለመፍጠር  ዘላቂ የጤና ልማት ግቦችን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ኢትዮጵያ እያደረገች ያለዉን ጥረት አሜሪካ እያደረገች ያለዉን ድጋፍ  አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል። 


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ረዳት ጸሐፊ ዶ/ር ማማዲ ይላ፣ የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ ለመደገፍ ያለውን የላቀ ቁርጠኝነት ገልጸው፤ በቀጣይም እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ለማገዝ እና ለማጠናከር ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።


በመጨረሻም፣ልዑካን ቡድኑ በጤና ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት የተደራጁ የዲጂታል ጤና፣ የኢኖቬሽን፣ የጤና መረጃና ምክክር፣ እንዲሁም የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስቱዲዮዎችን በመጎብኘት በየዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ስራዎችን ተመልክተዋል።