Articles

76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ጉባኤ በአዲስ አበባ አደዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀመረ 

WHO

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ጉባዔ አዲስ አበባ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ የመክፈቻ መርሃግብር በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት መካሄድ ጀምሯል። 


በመድረኩ ከ40 በላይ የአፍሪካ ሃገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ተወካዮች የዓለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት፣ ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

13ኛው የምስራቅ አፍሪካ ጤና ፌዴሬሽኖች ጉባኤ እና ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን በአድዋ ሙዚየም “ፅናት፡ የምስራቅ አፍሪካን የጤና ኢኮኖሚ መገንባት!” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል

13th East African Health Federations Conference

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጉባኤው የመክፈቻ  መልዕክታቸው ከ130 ዓመታት በፊት ቀደምት ኢትዮጵያውያን በዓድዋ በአይበገሬነት ያስመዘገቡት ድል፣ ዛሬ የሕዝባችንን ጤና በራስ አቅም የመጠበቅ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ መደገም አለበት ብለዋል።

የጤና ሉዓላዊነት ማለት መድኃኒቶችንና የሕክምና ቁሳቁሶችን በራሳችን የማምረት፣ የጤና ባለሙያዎቻችንን የማሰልጠንና የማቆየት፣ እንዲሁም ወረርሽኞችን ወይም የጤና ቀውሶችን የዓለምን እጅ ሳንጠብቅ በራሳችን የመቋቋም ብቃት መፍጠር መሆኑን አቶ ተመስገን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጤናው ዘርፍ የግል ባለሀብቶች ከመንግሥትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው የሚሠሩበት አህጉራዊ መድረክ እንዲኖር፣ የአፍሪካ ጤና ፌዴሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ እንዲመሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የሚያካሂደው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ጉባዔ ዝግጅት በተመለከተ በፕ/ር መሃመድ ጃናቢ የተመራ የዓለም ጤና ድርጅት ልዑካን ቡድን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር ተወያይቷል

World Health Organization

በጉባዔው እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዘግጅቶችን፣ የጊዜ ሰሌዳ እና ጉባዔው ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለልኡካን ቡድኑ ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር መቅደስ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ቀጠናዊ ጉባዔውን በኢትዮጵያ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ለጉባኤው የተደረጉ ዝግጅቶችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የገለጹት ፕ/ር መሃመድ፤ ጃናቢ በበኩላቸዉ የደህንነት፣ የአዳራሽ ዝግጅት እና የትራንስፖርት አቅርቦት በመልካም ሁኔታ መዘጋጀቱን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ አንደሚካሄድ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ስጋቶች እና የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ቁጥጥር በተመለከተ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በጉባዔው የሚነሱ የአፍሪካ የጤና ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ጉባዔ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት እና ከአለም አቀፍ ድርጅቶች የተወከሉ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡