በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአከርካሪ ቀዶ ህክምና ማዕከል /National spine center/ ስራ ጀመረ 

  • Time to read less than 1 minute
St. Paul

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ግቢ የተገነባዉ የአከርካሪ ቀዶ ህክምና ማዕከል /National spine center/ የጤና ሚኒስትር እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል ም/አምባሳደር፣ የጄዲሲ መስራችና አንጋፋ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የቅዱስ ጳውሎስ አመራሮች እንዲሁም በርካታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።


ማዕከሉ እውን እንዲሆን ድጋፍ ለደረገዉ  በአሜሪካዊ እስራኤላውያን /American Jewish Joint distribution Commitee_ JDC/ እና ሌሎች አካላት ምስጋና ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ሕይወት የሚቀይሩ ቀዶ ህክምናዎች ግለሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብና በማህበረሰብም የሚያመጣው ለውጥ ትልቅ እንደሆነ በመናገር፣ የጤና ሚኒስትር የነርቭ እና የጀርባ አጥንት ቀዶ ህክምናና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት፣ የማገገሚያ ስርአቶችን ለማጠናከር፣ እና እነዚህን አገልግሎቶች በአገር አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት የሚያስቀጥል የባለሙያ ኃይል ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።


የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነትና ትብብር ከጤና ዘርፍ በተጨማሪ በበርካታ ዘርፎች መሆኑን የጠቆሙት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የእስራኤል ም/አምባሳደር ቶመር ባርላቪም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆነን ሰዎችን በመርዳት ላይ በመሆናችን ደስተኛ ነን ብለዋል።