"ጤናን ጨምሮ የዜጎቻችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የምናረጋግጠው በመደጋገፍ እሳቤ ነው" አቶ አሻድሊ ሀሰን - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጤናው ዘርፍ የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ማስጀመርያ መርሀ ግብር ተካሄዷል። በዚህም የቤት እድሳት፣ የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ፣የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን እንደተናገሩት በክልሉ በሚደረጉ ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቅሳሴዎች ውስጥ ጤና ዋነኛው መሆኑን ጠቁመው የክልሉን ማህበረሰብም የጤና አገልግሎት ለማሻሻል እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰሩ ላሉት ተግባራት ጤና ሚኒስቴር እያደረገ ላለው ድጋፍ በክልሉ መንግስትና ህዝብ አመስግነዋል።
ጤናን ጨምሮ የዜጎቻችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የምናረጋግጠው በመደጋገፍ እሳቤ እና በጋራ ተቀናጅተን መስራት ስንችል ነው ብለዋል ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሀሰን።