የአውሮፓ - የአፍሪካ ህብረት ለአፍሪካ ጤና አጋርነት ከ100 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የድጋፍ ፓኬጆች ይፋ ሆኑ

  • Time to read less than 1 minute
EU-African Union

የአፍሪካን የጤና ደኅንነት፣ ጽናትና ሉዓላዊነት በማጠናከር ረገድ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአፍሪካ-አውሮፓ ህብረት የጤና አጋርነት የድጋፍ ፓኬጆች በሶስት አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።

ጠንካራ ስርዓት፣ ጠንካራ ተቋማት እና ለማህበረሰቡ የተሻሉ የጤና ውጤቶች እንዲመጡ ከአፍሪካ ሲዲሲ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከሁሉም አጋሮች ጋር በቅርበት ለመስራት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነች ብለዋል የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።

ሁለቱ አህጉራት የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት እና ሰፊ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ወቅታዊና የወደፊት የጤና ስጋቶችን ለመቅረፍ እየተደረገ ያለውን ጥረት በመቀጠል የአፍሪካ - የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል ሲዲሲ የረጅም ጊዜ እና አጠቃላይ የጤና አጋርነታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ጠቁመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ጆዜፍ ሲኬላ የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር፣ ዶ/ር ጄን ካሴይ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር፣ የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ከፍተኛ ተወካዮች እንዲሁም አለም አቀፍ የጤና አጋሮች በመድረኩ ተገኝተዋል።