የእናቶችና ህፃናት ጤና
The Maternal, Child Health and Nutrition (MCHN) directorate is one of the Directorates under the State Minister's office for Programs.
- Read more about የእናቶችና ህፃናት ጤና
- 1165 views
The Maternal, Child Health and Nutrition (MCHN) directorate is one of the Directorates under the State Minister's office for Programs.
ለጤናማ ፣ የበለፀጉ እና አምራች ኢትዮጵያውያን የድንገተኛ የጤና አገልግሎት ስርዓትን ማላቅ።
በአጣዳፊ ህመም የታመሙ እና በድንገተኛ አደጋ የተጎዱን እንክብካቤ የሚያሻሽል እና ለየተባበረ የጤና አገልግሎት (UHC) እውንነት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ጠንካራና የተባበረ ስርዓትን በሁሉም ደረጃዎች በመገንባት ፍትሃዊ ፣ የተቀናጀ፣ ያልዘገየና ጥራት ያለው የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህክምና አገልግሎት መስጠት።
Disease Prevention and Control Directorate is responsible to coordinate communicable and non-communicable disease programs. Accordingly, the Directorate coordinates the designing and development of national strategies, policy guidance, technical guidelines, protocols, Standard Operating Procedures, and intervention packages. Moreover, the Directorate is responsible for ensuring the availability and uninterrupted supply of commodities for the programs, which is mainly done in collaboration with the Ethiopian Pharmaceuticals Supply Agency (EPSA).
በሁሉም የጤና ተቋማት ውስጥ ሁሉም ሰው በተቻለ መጠን የተሻለ አገልግሎትና ጤና እንዲኖረው
ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን በመፍጠር ጤናንና የጤና አገልግሎቶችን ማሻሻል እና በሁሉም ሆስፒታሎች ላይ የማህበረሰብ እምነትን ማዳበር።
ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በሃይማኖታቸው ፣ ጎሳቸው ፣ ማህበራዊ ደረጃቸው ፣ ዕድሜያቸው እና ጾታቸው ሳይለያዩ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለመፍጠር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሥርዓቶችን ማዘጋጀት።
የሕክምና አገልግሎቶች ዳይሬክቶሬት ዓላማ የጤና አገልግሎት ጥራትንና የሕዝቡን አጠቃቀም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን እንደገና በማደራጀት ማሻሻል ነው።
የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት (WCYAF) ከሌሎች ዳይሬክቶሬቶች ፣ ከፌዴራል ሆስፒታሎች፣ ከኤጀንሲዎች እንዲሁም ከክልልና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ መዋቅሮች ጋር በቅርበት በመስራት አብዛኛዎቹን የሥርዓተ-ፆታ ፣ የሕፃናት ፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ሥራዎችን የማስተባበርና የመምራት ኃላፊነት አለበት። በዚህም የሴቶች፣ ወንዶች ፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞችን የጤና አገልግሎት እኩል ተጠቃሚነት ያረጋግጣል::
ዳይሬክቶሬቱ በሁሉንም የጤና ስርዓት ደረጃዎች ላይ ከ ሥርዓተ-ፆታ፣ ሕፃናት ፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ጋር የተዛመዱ ጉዳዮች ተገቢ ትኩረት መሰጠቱን ለማረጋገጥ ሁሉንም መዋቅሮቹን (4 የፌዴራል ሆስፒታሎች ፣ 7 ኤጀንሲዎች እንዲሁም 2 የከተማ አስተዳደር እና 10 የክልል ጤና ቢሮዎች ) ሲደግፍ ቆይቷል።
በኢትዮጵያ ቀልጣፋ ፣ ዘላቂ እና ፍትሃዊ የጤና ፋይናንስ ለማየት።
የጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሳካት ሀብቶችን መለየት ፣ማሰባሰብ፣ ማንቀሳቀስ ፣ መመደብና በአግባቡ መጠቀምን ለማረጋገጥ ከሚኒስቴሩ ሌሎች ዳይሬክቶሬቶች፣መንግሥት ድርጅቶች ፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች ጋር ቅንጅትንና አጋርነትን መመስረት።
• ዳይሬክቶሬቱ የጤና አገልግሎት ፋይናንስ ስትራቴጂን የመተግበር እና የመምራት ኃላፊነት አለበት።
• የአዳዲስና የነባር ጣልቃ ገብነቶች ወጪ ቆጣቢነትን የመገምገምና የማረጋገጥ ሚና አለው።
የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የስራ ሂደት የጤናዉን ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን፤ ተደራሽነትን እና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል፤ አገር በቀልና አዳዲስ ፈጠራ የታከለበት(innovative) በሆኑ ቴክኖሎጂዎች እየታገዘ የጤና አገልግሎትን መተግበር፤ መረጃን በወቅቱ፣በጥራት ለመሰብሰብ፣ ለመጠቀም እና ለማስተላለፍ የሚያስችል የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
የሥራ ሂደቱ እንደ አጠቃላይ ከሚተግብራቸዉ ግቦች መካከል ዋናዎቹ እንደ ወጪ ቆጣቢ፣ አገር በቀል እና በፈጠራ ላይ የተመሰረቱ የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመቀመር ከአገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራት እና ፍትሃዊነትን ወደ ላቀ ሁኔታ ማሻገር ነዉ፡፡
የዳይሬክቶሬቱ ዓላማ የሚኒስቴሩን ኦፕሬሽኖችና የውስጥ ቁጥጥር ሂደቶች፣ የአደጋ አስተዳደርና የአመራር ሂደቶችን እሴት ለመጨመርና ለማሻሻል የተነደፉ ገለልተኛና ተጨባጭ የምክር አገልግሎት መስጠት ነው።
የዳይሬክቶሬቱን እንዲሁም የሚኒስቴሩን ዓላማ ለማሳካት ዳይሬክቶሬቱ ከኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት የገንዘብ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/2009 እና የፋይናንስ አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 190/2010 ጋር በሚጣጣም መልኩ የሚከተሉት ዋና ኃላፊነቶች አሉት።
በድርጅት አስተዳደር ላይ ማተኮር ለዳይሬክተሩ የበለጠ ንቁ እና ስትራቴጂያዊ ቡድን ተጫዋች የመሆን እድልን ይሰጣል። ለዚህም በሚኒስቴሩ የአስተዳደር ሂደት ውስጥ የዳይሬክቶሬቱ ኃላፊነቶች የሚከተሉት ናቸው፡
የሚኒስቴሩን የአስተዳደር ሂደት ለማሻሻል ለአመራሩ ተገቢውን የውሳኔ ሃሳብ መገምገምና ማቅረብ፤
የማንኛውም ተቋም የመንግስትም ይሁን የግል ስኬት በስሙ ላይ በእጅጉ የተመካ ነው። የተገልጋዮች፣ የሰራተኞች ፣ የባለሀብቶች ፣ የፖሊሲ አውጪዎች እና የመገናኛ ብዙኃን አስተያየቶች በአንድ ድርጅት ብልጽግና ላይ ኃይለኛ ተፅእኖ አላቸው። ስለ ተቋሙ ያላቸው ግንዛቤ ከተቋሙ ጋር መሥራትና መደገፍ ይፈልጉ እንደሆነ ውሳኔዎቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት የድርጅትን ስም ለመገንባት፣ ግንዛቤን እና ድጋፍን ለማግኘት እንዲሁም በሕዝብ አስተያየትና ባህሪ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ጠንካራ የግንኙነት መስመር አስፈላጊነት የማይካድ ነው።