በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች በተደረገ ከሀያ አራት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይን ሕክምና ድጋፍ ከሶስት ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የአይን ቀዶ ጥገና ህክምና መስጠት መቻሉ ተገለጸ፡፡
የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት በአይን ህክምና ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ከሃያ አራት ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ በማሰባሰብና የህክምና ባለሙያቸው ድጋፍን በማቀናጀት በአፋር እና በአማራ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ህክምና ሳያገኙ የቆዩ ከሶስት ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የአይን ሞራ ግርዶሽ የነጻ ህክምና መስጠት መቻሉን እና የህክምና ተቋማቱም በመደበኛ አገልግሎታቸው ህክምናውን መስጠት የሚያስችላቸው ስራ መከናወኑን የጤና ሚኒስትር የበሽታ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሕይወት ሰሎሞን አስታወቁ፡፡