በጉባዔው እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዘግጅቶችን፣ የጊዜ ሰሌዳ እና ጉባዔው ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለልኡካን ቡድኑ ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር መቅደስ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ቀጠናዊ ጉባዔውን በኢትዮጵያ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ለጉባኤው የተደረጉ ዝግጅቶችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የገለጹት ፕ/ር መሃመድ፤ ጃናቢ በበኩላቸዉ የደህንነት፣ የአዳራሽ ዝግጅት እና የትራንስፖርት አቅርቦት በመልካም ሁኔታ መዘጋጀቱን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ አንደሚካሄድ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ስጋቶች እና የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ቁጥጥር በተመለከተ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በጉባዔው የሚነሱ የአፍሪካ የጤና ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ጉባዔ ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት እና ከአለም አቀፍ ድርጅቶች የተወከሉ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡