Articles

"የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማሳደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጡ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ

lia

አገር አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው የስራ አቅጣጫ የሰጡት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ እንደተናገሩት የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማሳደግ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጡ ስራ በ2014 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡


የጤና መድህን አባላትን ቁጥር በማሳደግና ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ ስርዓትን በመፍጠር በጤና ተቋማት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚረዳ የገለጹት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ ይህንን ለማሳካትም ከላይ እስከታች ያለው የጤና መዋቅር አመራር በመደጋገፍና በቅንጅት መንፈስ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡

ፖሊዮን ጨርሶ ለማጥፋት የሚያስችል የክትባት ዘመቻ  በይፋ ተጀመረ

Dr. Dereje Duguma

ከፖሊዮ ነጻ የሆነ አለም እንፍጠር በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በሲዳማ ክልል በአዋሳ ከተማ እና በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን ዲላ ከተማ የክትባት ዘመቻ መርሀግብር ያስጀመሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ  በመርሀግብሩ እንደተናገሩት የጤና ሚኒስቴር ፖሊዮን ለማጥፋት በመደበኛ ክትባትና በዘመቻ በሚሰጥ ክትባት ከሀገራችን  ለማጥፋት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።


ባለፉት አመታትም በተከናወነው ስራ ፖሊዮን ማጥፋት ተችሎ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት  በተለያዩ አከባቢዎች  እየታየ ያለውን የልጅነት ልምሻ በሽታ ለማጥፋትም እስከ ጤና ኬላ በተዘረጋ መዋቅር እና ከአጋር አካላት ጋር በተቀናጀ አሰራር እየተተገበረ መሆኑን ተናግረው  ይህም መንግስት ለሕጻናት ጤና መሻሻል ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

በጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች እውቅና ተሰጣቸው

youth

የጤና ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወጣቶች በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር በጤናው ዘርፍ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡ 


እውቅናውን  የተሰጣቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች ሲሆኑ በቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል፣ በአለርት ማእከል፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በጥሩነሽ ቤልጂንግ  ሆስፒታል፣ በካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ፣ በራስ ደስታ ሆስፒታል እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ወስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ ወጣቶች ናቸው፡፡


የእውቅና አሰጣጥ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ እንደ ጤና ሴክትር ብዙ ነገሮችን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ማሳካት በማንችልበት አገር ውስጥ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት  መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡