Articles

የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ ሊካሄድ ነው!

covid19

ጤና ሚኒስቴር ከመምህራት ማህበር ጋር በመሆን የኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ ውጤታማ በሚሆንበት  መንገድ ዙሪያ በአዳማ እየመከረ ነው፡፡  


የፀጥታ ችግር በሌለባቸው የአገራችን ክፍሎች ከ12 ሚሊዮን በላይ ዶዝ ለመከተብ የታሰብ ሲሆን በተለይም በትምህርት ቤት እና በዩኒቨርስቲዎች ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የጤና ሚኒስቴር የክትባት ባለሙያ አቶ ተመስገን ለማ ተናግረዋል፡፡


በክትባት ዘመቻው እድሚያቸው ከ18 አመት በላይ የሆነ ማንኛው ሰው እና በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንን የመከተብ ስራ እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልፃል፡፡


ከኮቪድ-19 የክትባት ዘመቻ በተጨማሪ በቀጣይም የማህፀን በር ካንሰር ክትባት በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች እድሚያቸው ከ14 አመት ለሆናቸው ልጃገራዶች ክትባቱን ለመስጠት የዘመቻ ስራ እንደሚጀመር አቶ ተመስገን ለማ ጠቁመዋል፡፡

በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው 23ኛ የጤናው ዘርፍ ጉባኤ ተሳታፊ የነበሩ ሁሉም ታዳሚዎች የኮቪድ 19 ምርመራ እንደተደረገላቸው ተገለጸ።

RDT test

ይህም በርካታ ቁጥር ያለው ተሳታፊ ለሚገኝባቸው ወሳኝ  ሀገራዊ ሁነቶች  ምሳሌ የሚሆን ተግባር መሆኑ ተነግሯል። 
"ፈጣን ምላሽ ሰጪ የጤና ስርአት በአዲስ ምእራፍ" በሚል መሪ ቃል  የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መዲና በሆነችው ጅግጅጋ  ሲካሄድ የሰነበተው የጤናው ዘርፍ ጉባኤ ሁሉም ተሳታፊዎች ከጉባኤው  አንድ ቀን አስቀድሞ የኮቪድ 19 ምርመራ የወሰዱበትና ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ተሳታፊዎች የተገኙበት እንዲሁም ሌሎችም  ሁሉም የጥንቃቄ መንገዶች የተተገበሩበት እንደሆነ ገልጸው  ለሌሎች ተመሳሳይ ሀገራዊ ሁነቶች ትምህርት የሰጠ እንደነበር ተሳታፊዎች ተናግረዋል። 

የጤና ሚኒስቴር በአዲስ መልክ ያበለፀገውን ዌብ ሳይት ይፋ አደረገ

website

አዲሱ ዌብ ሳይት ሁለገብና መረጃዎችን በተደራጀና ሳቢ በሆነ መንገድ ለተጠቃሚዎችና ለባለድርሻ አካላት የሚያደርስ መሆኑን የገለፁት ዌብ ሳይቱ እውን መሆኑን ያስተዋወቁት በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ዳንዔል ገብረሚካኤል ናቸው።


የቀድሞው ዌብ ሳይት መረጃ እንደልብ የማይገኝበትና ሳቢ እንዳልነበረ ቅሬታ የሚቀርብበት ነበር ያሉት ዶ/ር ዳንዔል አዲሱ ዌብ ሳይት በተገቢ መረጃዎች የተደራጀና ለአጠቃቀም ሳቢ እና ቀላል ሆኖ የቀረበ ሲሆን ማንኛውም  ከሀገር ዉጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ተገልጋዮች የኢ ላይብረሪ ፣ኦን ላይን የበጎ ፈቃድና ልገሳ አገልግሎት፣ የአስተያየት/ቅሬታ ማቅረቢያ፣ የቴሌቪዥን ቻናል፣ የዲጂታል ጤና ሲስተሞች፡ የጤና ማህበራት የጥናትና ምርምር ውጤቶችን እና ሌሎችንም ያካተተ መሆኑ ተገለጿል።