Articles

የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ተጀመረ

Breast cancer

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ በፈረንጆች ጥቅምት ወር የሚደረገው የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ በፓዮኒር ምርመራ ማዕከል ከመስከረም 20 ጀምሮ ለአንድ ወር በነፃና በግማሽ ክፍያ በሚሰጥ ምርመራ ተጀምሯል።


በየዓመቱ 40 ሺህ ያህል ሰዎች በጡት ካንሰር ምክንያት እንደሚሞቱ የጠቆሙት በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር መሠረት ዘላለም ካንሰር ስር ከሰደደ በኋላ ለማከም የሚያደርሰውን የጤና፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስና ለመከላከል ቀድሞ በመመርመር የጤናን ሁኔታ ማወቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በቪየና ኦስትሪያ በተካሄደዉ 66ኛው የIAEA ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

Ethiopian delegation

"በኑክሌር መስክ ዓለም አቀፍ ትብብር!" በሚል መሪ ቃል  በቪየና ኦስትሪያ በተካሄደዉ 66ኛው የIAEA ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ተሳትፈዋል፡፡


በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት በቪየና ኢንተርናሽናል ሴንተር (VIC) በቪየና ኦስትሪያ የተካሄደዉ ይህ ጉባኤ ከኒዩክሌር ቴክኖሎጂ እና ሳይንስ ዙሪያ ለህክምና አገልግሎት ጥቅም የሚዉሉ ቴክኖሎጂዎችን በተለይም የካንሰር ጨረር ህክምናን ጨምሮ ለተለያዩ ህክምና ዘርፎች ጥቅም ላይ በሚዉሉ የኑክሌር ቴክኖሎጂ እና ሳይንስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

   
በ66ኛው የIAEA ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ተወካዮች ከአክሽን ፎር ካንሰር ቴራፒ (PACT) መርሃ ግብሮች ቡድን ጋር በቀጥታ ውይይት በማድረግ በኢትዮጵያ እና በIAEA መካከል ስላለው እና የወደፊት የቴክኒክ ትብብር በተመለከተም ተወያይተዋል። 

የእናቶችና የህፃናት ጤናን ለማሻሻል የሚያግዙ 10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮችን ለመለገስ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

mobile medical

የጃፓን መንግስት በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን ፍትሃዊና ተደራሽን ለማጠናከር የሚያግዙ የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ ያላቸው 10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮችን ለመለገስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል

በጃፓን መንግስት በኩል ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታኮኮ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራቸው የተደረገው የ500 ሚሊዮን የጃፓን የን/3.5 ሚሊዮን ዶላር/ ድጋፍ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ክልሎች ድጋፍ የሚሹ ተብለው በተለዩት በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች ያለውን የእናቶችና ህፃናት ጤና በማሻሻል የሚሞቱ እናቶችና ህፃናትን ቁጥር እንደሚቀንስ ያላቸውን ተስፋ ጠቁመው ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮቹ አልትራሳውንድና ኤሌክትሮ ካርዲዮግራፍን ጨምሮ መሰረታዊ የህክምና ቁሳቁሶችን ያሟሉ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡