የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት
በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በፕሮግራሙ ክንፍ ስር ከሚገኙት ዳይሬክቶሬቶች መካከል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት አንዱ ነው። የዳይሬክቶሬቱ ዋና ሚናዎች እና ኃላፊነቶች አስፈላጊ መመሪያዎችን እና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት እንዲሁም ለሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ እና በመከታተል ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ዕውን ማድረግ ነው።
ዳይሬክቶሬቱ በሰሩ 3 የጉዳይ ቡድኖች አሉት፤ እነሱም የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም እና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ጉዳይ ቡድን ፣ የጤና ትምህርት እና ማስተዋወቂያ ጉዳይ ቡድን እንዲሁም የጤና ማዕከል ተሃድሶ ጉዳይ ቡድን ናቸው። የእያንዳንዱ ጉዳይ ቡድን ሚናዎች እና ኃላፊነቶች እንዲሁም ፕሮግራሞች፣ ፕሮጄክቶችና ተነሳሽነቶች ከዚህ በታች ተብራርተዋል።