ለፖሊሲ ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
ራዕይ
በማስረጃ ላይ በተመሰረተ ዕቅድ እና ውሳኔ አሰጣጥ አማካኝነት የሕዝቡን የተሻሻለ የጤና ሁኔታ ለማየት
ተልዕኮ
በጤናው ዘርፍ ተግባራዊ የሆነ አንድ ዕቅድ ፣ አንድ ሪፖርትና አንድ በጀት መርሆዎችን ተቋማዊ በማድረግ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ዕቅድንና ውሳኔ አሰጣጥን ማሳደግ። እነዚህ በዋነኝነት የሚፈፀሙት ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽነትንና አጠቃቀምን በማሻሻል ፣ በሁሉም ደረጃ የመረጃ አስተዳደር አቅምን በማሻሻል ፣ የክትትል እና የግምገማ አሰራሮችን በማሻሻል ፣ መደበኛ የመረጃ ማሰባሰብ እና የሪፖርት ስልቶችን ስታንዳርዳይዝ በማድረግ፣ ጥናቶችን እና ግምገማዎችን በማካሄድ ነው።
ዳራ
ለፖሊሲ ዕቅድ ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬቱ በሚኒስቴር ደረጃ ከሚገኙ ዋና የሥራ ሂደቶች አንዱ ሲሆን የፖሊሲ ፣ የዕቅድ ፣ የክትትልና የግምገማ ሥራዎችን የማስተዳደር ዋና ኃላፊነት ያለበት ነው።