ችላ የተባሉ የትሮፒካል በሽታዎች (NTDs) ፕሮግራም

NTD

ችላ የተባሉ የትሮፒካል በሽታዎች (NTDs) በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ላይ ከባድ ህመም የሚያስከትሉ የጥገኛ ህዋስና የባክቴሪያ በሽታዎች ስብስብ ናቸው። የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለስምንት በሽታዎች የህዝብ ጤና ላይ ባላቸው ተፅእኖ መሰረት ቅድሚያ ሰጥቷል። እነዚህም ዓይን ማዝ(ትራኮማ) ፣ በአፈር የሚተላለፉ ሄልሚንትስ (STH) ፣ ሺስቶማሲያሲስ፣ ሊምፋቲክ ፊላሪያሲስ (LF) ፣ ኦንኮሴርካ(ኦንኮ) ፣ ድራንኩላ/ጊኒዎርም (GWD) ፣ ቁንጭር(ሌሽማንያሲስ) እና ፖዶኮኒኦሲስ ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት(WHO) ስኬቢስን እንደ አንድ NTD በቅርቡ እውቅና ሰቶታል።

ብሔራዊ የወባ ማስወገጃ ፕሮግራም (NMEP)

malaria

ብሔራዊ የወባ ማስወገጃ ፕሮግራም(NMEP) በበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ስር ከሚገኙት ፕሮግራሞች መካከል በአንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ከወባ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ጣልቃ ገብነቶችን እና እንቅስቃሴዎችን የመንደፍ፣የማቀድ ፣ የመተግበር ፣ የመከታተል እና የመገምገም ኃላፊነት አለበት።

 

የ NMEP ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

  • የፀረ ወባ ጣልቃ ገብነቶችን መንደፍ ፣
  • የቴክኒክ መመሪያዎች፣ ማኑዋሎች ፣ፕሮቶኮሎች ፣መደበኛ የአሰራር ሂደቶች፣ እና የፈንድ ፕሮፖዛሎችን ማዘጋጀት እንዲሁም የንዑስ-ብሄራዊ የፕሮግራም ክፍሎችንና የሠራተኞችን አቅም መገንባት።
  • የፀረ ወባ መድሐኒቶችን እና የፀረ-ተባይ ውጤታማነት ከምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር መከታተል
  • የጣልቃ -ገብነት ተፅእኖን መለካት

 

ብሔራዊ የኤች አይ ቪ/ኤድስ እና የጉበት ቫይረስ መከላከል እና ቁጥጥር

HIV

ብሔራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራም በበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ስር ከሚገኙት ፕሮግራሞች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የኤችአይቪ እና የጉበት ቫይረስ ተዛማጅ ጣልቃ ገብነቶችንና እንቅስቃሴዎችን ዲዛይን የማድረግ፣ እቅድ የማውጣት፣ የመተግበር፣ የመከታተል እና የመገምገም ኃላፊነት አለበት።

ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

  • ጣልቃ ገብነቶችን መንደፍ ፣
  • የቴክኒክ መመሪያዎችን ፣ ማኑዋሎችን ፣ ፕሮቶኮሎችን እና መደበኛ የአሰራር ሂደቶችን ማዘጋጀት እንዲሁም የንዑስ-ብሔራዊ የፕሮግራም ክፍሎችን እና የሠራተኞች አቅም መገንባት።
  • ከEPHI ጋር በመተባበር የቫይረስ ብዛትን መከታተል፣ የ ARV መድኃኒቶች ውጤታማነት እና የጣልቃ ገብነት ተፅእኖን መለካት።

 

ፕሮግራሞች፣ ፕሮጄክቶች እና ተነሳሽነት

ፕሮግራሙ ለኤችአይቪ/ኤድስ እንዲሁም ለጉበት ቫይረስ ፕሮግራም የተለየ ብሔራዊ ስትራቴጂክ ዕቅድ አለው።

የአእምሮ፣ የኒውሮሎጂ እና የአደንዛዥ ዕፅ ፕሮግራም

mental health

ብሔራዊ የአዕምሮ፣ የኒውሮሎጂ እና የአደንዛዥ የጤና ፕሮግራም (NMNSP) በበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ስር ከሚገኙት ፕሮግራሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ስታንዳርዶችን የማዘጋጀት፣ ብሔራዊ መመሪያዎችን የማዘጋጀት እና የመከለስ ፣ አላማ ማስቀመጥን ጨምሮ ብሔራዊ የድርጊት ዕቅዶችን የማዘጋጀት፣ ለአቅም ግንባታ አስፈላጊ ሀብቶችን የማሰባሰብ፣ የመከታተል፣ የግንዛቤ ፈጠራ እና ግምገማ፣ የአድቮኬሲ እና የአሠራር ምርምር፣ እና የአዕምሮ ጤና አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞች አጠቃላይ ብሔራዊ ቅንጅትን የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት።

ግብ

የአእምሮ ደህንነትን ማጎልበት፣ የአእምሮ ሕመሞችን መከላከል፣ የአእምሮ ጤንነት ችግር እና የስነልቦና ጉድለት ያለባቸው ሰዎችን እንክብካቤ መስጠት እና የማገገም ሂደትን ማሻሻል።

ፕሮግራሙ በ 2014 G.C የmhGAP ፕሮግራምን እና ሁለተኛውን ብሔራዊ የአእምሮ ጤና ስትራቴጂ ዕቅድ ማስፋፊያ ተግባራዊ አድርጓል።

 

የታዳጊዎች እና ወጣቶች ጤና ፕሮግራም

AYCN

የሕዝብ ብዛት በኢትዮጵያ

በ 2016 የኢትዮጵያ ማዕከላዊ እስታቲስቲክስ ኤጀንሲ (CSA) የሕዝብ ትንበያ መሠረት ከ 10 እስከ 29 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች እና ወጣቶች ቁጥር 38,545,711 (19,466,543 ወንዶች እና 19,079,177 ሴቶች) ናቸው። ይህ የዕድሜ ቡድን ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ 42 በመቶ የሚገመት ሲሆን ከ 10 እስከ 24 ዕድሜ ያላቸው ደግሞ 33 ከመቶው ናቸው። አብዛኛው የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች እና ወጣቶች በገጠር ይኖራሉ (ከወንዶች 79 በመቶ እና 78 በመቶ ሴቶች)። በወጣት የዕድሜ ክልል ውስጥ ካሉት መካከል በገጠር አካባቢ የሚገኙት የአነስተኛ ዕድሜ ታዳጊዎች ቁጥር ይጨምራል። ከ 10 እስከ 14 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ከ 81-82 በመቶ የሚሆኑት በገጠር የሚኖሩ ሲሆኑ ከ 25 እስከ 29 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 74-75 በመቶ የሚሆኑት በገጠር የሚኖሩ ናቸው። በኋለኞቹ ዕድሜዎች የከተማ ነዋሪዎች የመጨመር አዝማሚያ በጉርም

የቤተሰብ ዕቅድ

Family Planning

የቤተሰብ ዕቅድ ጉዳይ ቡድን ለሀገሪቱ የጤና ኢንዴክሶች መሻሻል እንዲሁም ከጤና ጋር የተዛመዱ ዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) ስኬት ላይ አስተዋፅኦ በማድረግ ጉልህ እና ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

 

ተልዕኮ

የጉዳዩ ቡድን ተልዕኮ “የጥራት አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ እና ግለሰቦች እና ማህበረሰቦችን ስለ ጤንነታቸው በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ እንዲሰጡ ፣ በዚህም የኢትዮጵያውያንን ጤናማ የአኗኗር ዘይቤና የኑሮ ጥራት ከፍ ለማድረግ” ነው።

የእናቶች ጤና

Maternal Health

በኢትዮጵያ የእናቶች ጤና አጠቃላይ እይታ

ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት በእናቶች ሞት ላይ አስገራሚ ለውጥ አድርጋለች፣ MMR በ 2000ዓ.ም 871 ከ100,000 የነበረ ሲሆን በ2017ዓ.ም  ወደ 401 ከ100,000 ቀንሷል፤  ይህ በየዓመቱ ወደ 12,000 የእናቶች ሞት ነው። ቀጥተኛ የወሊድ ችግሮች 85% የሚሆኑት የሞት መንስኤዎች ናቸው። የረጅም ጊዜ ሁኔታዎች ሴቶች ላይ ከወሊድ ጋር የተዛመዱ በሽታዎችን አስከትለዋል። ለምሳሌ ፊስቱላ ፣ የማሕፀን ተፈጥሯዊ ቦታ መዛባት፣ ሥር የሰደደ የወገብ አጥንት ህመም ፣ ድብርት እና ድካም። በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ፊስቱላ የተለመደ ሲሆን በዋነኝነት በልጃገርረድ ዕድሜ ከሚፈጠር እርግዝና እና ችላ ከተባለ ረዥም ምጥ ጋር ተዳምሮ የሚፈጥረው ነው። ከፍተኛ የእናቶች ሞት መጠን በቀጥታ ከ ከፍተኛ የአራስ ሕፃናትሞት መጠን (29/1,000 በህይወት የተወለዱ ህጻናት )ጋር ይያያዛል። ይህ በወሊድ ጊዜ እናቶቹ የነበሩበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያንፀባርቃል። ለአራስ ሕፃናት ሞት ዋነኛ መንስኤ

ብሔራዊ የአመጋገብ ፕሮግራም

nutrition

መግቢያ

በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት አስርት ዓመታት የምግብ እጥረትን በመቀነስ አበረታች እድገት ተመዝግቧል። ሆኖም ነባር የምግብ እጥረት ደረጃ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ኢትዮጵያ አሁንም በአመጋገብ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቷን መቀጠል አለባት።

 

የተስፋፋ የክትባት መርሃ ግብር (EPI)

epi

የክትባት ፕሮግራም ወጪ ቆጣቢ ከሆኑ የጤና ጣልቃ ገብነቶች አንዱ ሲሆን አናሳ የህክምና ተደራሽነት ያላቸውና ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን በተረጋገጡ ስልቶች ያግዛል። በክትባት ሊከላከሏቸው የሚቻሉ በሽታዎች(VPD) ጋር የተዛመዱ ሕመሞችን እና ሞቶችን ከመቀነስ አኳያ የሚለኩ ስኬቶች ብሔራዊ የክትባት መርሃ ግብር በኢትዮጵያ በ1980G.C ከተጀመረ ጀምሮ ተመዝግበዋል። አዳዲስ እና በተገቢው መጠን ያላገለገሉ ክትባቶችን ደረጃ በደረጃ በማስተዋወቅ በክትባት ሊከላከሏቸው የሚቻሉ በሽታዎችን በመቀነስ አስደናቂ ስኬቶች ተገኝተዋል፤ እናም በአሁኑ የክትባት መርሃ ግብር ውስጥ የተካተቱ አጠቃላይ አንቲጂኖች ወደ አስራ ሁለት ደርሰዋል። አገሪቱ በክትባት እና የክትባት ሂደት ጉዳይ ላይ መርሃ ግብሩን የሚመራ ገለልተኛ የባለሙያ አካል የሆነውን ብሔራዊ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን (NITAG) አቋቁማለች። የ ቅንጅት ማስተባበሪያ ኮሚቴ (ICC) ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን በEPI ላይ የአጋር ትብብርን ለመደገፍ የቻሉ ቅንጅቶችን እና ዋና ውሳኔዎችን የማከናወን

የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ራዕይ

  • ጤናማ አምራችና የበለፀገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

  • ውጤታማ በሆነ መንገድ የጤና ሪፎርሞችንና የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በመተግበር፤ የተናበበና ተገልጋይ ተኮር ለውጥ አምጪ ተግባራትን በሀገር አቀፍ ደረጃ  በመፈጸም  የጤና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፡፡

አላማ

  1. የለውጥ አምጪና የእርስ በዕርስ የስራ ግንኙነት ተግባራት ውጤታማ በማድረግ የስራ አፈጻጸምን ማሻሻል  
  2. የዜጎች ቻርተርን ትግበራን በማጠናከር የዘርፉን የስታንዳርድ ትግበራ አቅምን ለማሻሻል 
  3. የአገልግሎት ማሻሻያ ጥምረትን በመተግበር የፕሮግራሞችን አፈጻጸም ማሻሻል 
  4. የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን፣ የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓትን፣ እንዲሁም የአመራር ተጠያቂነት ስርዓትን በመተግበር የዘርፉን ሀ