አቶ ገመቺስ መልካሙ ጎበና

Gemechis Melkamu
የዲጂታል ሄልዝ ሊድ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር

አቶ ገመቺስ መልካሙ ጎበና  በ 2004 ዓ.ም. በነቀምቴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኢንስትራክተርነት እና ጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ በመሆን ሙያዊ አገልግሎታቸውን የጀመሩ ሲሆን የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኒሽያን ተማሪዎችን በማስተማር እና በማማከር ረገድ  የነበረባቸውን ሃላፊነት በሚገባ ተወጥተዋል። የጤና ዘርፍ ምህዳሩን ለማሻሻል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከፍተኛ አቅም እንዳለው የተገነዘቡትም በዚህ ወቅት ነበር።


በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ የሥራ ልምድ ካገኙ እና ዲፓርትመንቱን በመምራት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በመጋቢት 2009 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ፣ የክልሉ የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በመሆን ቀጣይ ሃላፊነታቸውን ተቀብለው አገልግለዋል። በዚህ ቆይታቸው ውስጥ በወቅቱ የነበረውን  የሪሶርስ ውስንነት እና የሰው ሃይል አቅም ክፍተት በመቋቋም በክልሉ ያለውን የጤና መረጃ እና መሰረተ ልማት ለማሻሻል የነበረባቸውን ሃላፊነት በሚገባ ተወጥተዋል። 

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ ባስመዘገቡት ውጤት እና ባላቸው ሙያዊ ብቃት መነሻነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ  ጤና ሚኒስቴር ውስጥ የጤና መረጃ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  በመሆነው ከመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም የተመደቡ ሲሆን በመቀጠልም ከ2015 አመት ጀምሮ በአዲስ መልክ በተደራጀው የዲጂታል ሄልዝ ሊድ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
 

አቶ ገመቺስ ያላቸው ክህሎት እና አመራር አቅም በተለያየ የትምህርት ዝግጁነት እና ልምድ የተገነባ ሲሆን በዋናነትም በኮምፒዩተር ሳይንስ ኤምኤስሲ ዲግሪ ያላቸው  ሲሆን በተጨማሪም በሀገር ውስጥ በውጭ ሀገር በተለያዩ አጫጭር የአመራርና የቴክኒክ ስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ተሳትፏል።

Full Name: - Gemechis Melkamu Gobena
eMail :- gemechis.melkamu@moh.gov.et