አቶ እንዳልካቸው ፀዳል አለምነህ

Mr. Endalkachew
የጤናና ጤና ነክ ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ

አቶ እንዳልካቸው ፀዳል አለምነህ ከጥር ወር 2015 . ጀምሮ የጤናና ጤና ነክ ተቋማት እና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ በመሆን እያገለግሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘናና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ስር የጤና ባለሙያዎች ምዝገባ እና ፈቃድ ቡድን መሪ ሆነው ከሚያዝያ 2011 እስከ ታህሳስ 2015 ዓ.ም እንዲሁም ከታህሳስ ወር 2018 እስከ ሚያዚያ 2019 የፈተና ዝግጅት ኤክስፐርት በመሆን አገልግለዋል። በተጨማሪም አቶ እንዳልካቸው በጤናው ዘርፍ 12 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱ የፐብሊክ ሄልዝ ባለሙያ ናቸው። ከታችኛው የጤና መዋቅር ጀምሮ በኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት ጥሩ ልምድ ያላቸው በተለይም  የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ አሀድ (PHCU) ኃላፊ፣ የወረዳ ጤና ጥበቃ /ቤት ምክትል ኃላፊ እና የሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል።

ኢሜል: endalkachew.tsedal@moh.gov.et