"አለም አቀፍ ትብብር ወረርሽኞችን ለመከላከል ዝግጁነት እና ለጋራ ደህንነታችን መሰረታዊ ኢንቨስትመንት ነው።" ዶ/ር መቅደስ ዳባ

  • Time to read less than 1 minute
Pandemic Fund

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 21ኛው የፓንደሚክ ፈንድ (Pandemic Fund) የአስተዳደር ቦርድ ጉባዔ በአዲስ አበባ በይፋ ተጠናቋል። 

በጉባዔው የዓለም አቀፍ የጤና መሪዎች በዓለም ዙሪያ የበሽታዎችን ቅኝት፣ የላቦራቶሪ አቅምን እና የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ ስርዓቶችን ለማጠናከር የሚያችሉ ውይይቶች ተደርገዋል።

የጤና ሚኒስትር እና የቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጉባዔው የመዝጊያ ንግግራቸው አለም አቀፍ ትብብር ወረርሽኞችን ለመከላከል ዝግጁነት እና ለጋራ ደህንነታችን መሰረታዊ ኢንቨስትመንት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ መድረኩ የጋራ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳይ የተለየበት እና ድጋፎችን በመሬት ላይ ወደሚታይ ዘላቂ የአሰራር አቅም መቀየር የሚስችል ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ መቻሉን አክለዋል።