አቶ ቴዎድሮስ አበባው

Tewodros Abebaw
የጤና ባለሙያዎች ብቃት ምዘና እና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

አቶ ቴዎድሮስ አበባው ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በነርሲንግ BSc ዲግሪ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጠቅላላ የሕዝብ ጤና የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። በመንግስት ጤና ተቋም ውስጥ በነርስ ሙያ እና በተለያዩ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደ መምህር ፣ ረዳት መምህር፣ የመምሪያ ኃላፊ እና የአካዳሚክ ዲን በተለያዩ ጊዜያት ሰርተዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ከተቀላቀሉ ጀምሮ የፈተና አዘጋጅ ኦፊሰር፣ የፈተና አዘጋጅ ጉዳይ ቡድን መሪ እና የጤና ባለሙያዎች የብቃት ግምገማ እና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። በአሁኑ ወቅት አቶ ቴዎድሮስ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሥር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና እና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው።

 

ኢ-ሜይል፡tewodros.abebaw@moh.gov.et

ስልክ፡0115324189

ፋክስ፡0115516396