ወ/ሮ ፋጡማ ሰኢድ

Fatuma Seid
በጤና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ

ወ/ሮ ፋጡማ ሰኢድ በሐምሌ 2003 BSc፣ በሰኔ ወር 2018 ደግሞ በስነተዋልዶ ጤና ላይ የህዝብ ጤና ስፔሻሊስትነት የተቀበሉ ቁርጠኛ፣ ከፍተኛ ተነሳችነት ያላቸው እና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆኑ መሪ ናቸው።

ከጤና ጣቢያ፣ወረዳ ፣ዞን ፣ ከክልል እስከ ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ድረስ በሁሉም የጤና እርከን ሥርዓት አቋርጠው ከ 18 ዓመታት በላይ አገሪቷን እያገለገሉ ነው። በተለያዩ የአመራር ቦታዎች በወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ በዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና ኃላፊ እንዲሁም በክልል NTD መርሃ ግብር የሥራ ሂደት ባለቤት አገልግለዋል።

በMOH ውስጥ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ ለ 3 ዓመት ያህል በዞን የሴቶች ፌዴሬሽን  ምክትል ፕሬዚዳንት እና በቅርቡ የብሔራዊ የሴቶች መድረክ አስተባባሪ ናቸው። በቅርቡ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በ EPHI-PHEM ውስጥ የተመሠረተ ብሔራዊ EOC የጥበቃ ክፍል ሆነው በመበደብ ሰርተዋል። የሴቶች፣ ወጣቶች እና ህፃናት ጤንነት እና ተሳትፎ ላይ ትልቅ ተነሳሽነት አላቸው።

በአሁኑ ግዜ

  • በኢትዮጵያ ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው
  • በፌዴራል የሴቶች መድረክ ዘርፎች ውስጥ ሊቀመንበር ናቸው
  • በ GBV ብሔራዊ ግብረ ኃይል ውስጥ ተሰማርተዋል


ኢ-ሜይል፡fatuma.seid@moh.gov.et

ስልክ፡0115159653

ፋክስ፡0115516396