ወ/ሮ ኤደን ወርቅነህ ሳህለማርያም 

Eden Workneh
ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ወ/ሮ ኤደን ወርቅነህ በህዝብ ጤና የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በአጠቃላይ የህዝብ ጤና እና በሶሺዮሎጂ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው። ስራቸውን በደቡብ ክልል ገጠር ክፍል ውስጥ በጤና ጣቢያ የህክምና ሰራተኛነት/በጤና ጣቢያ ሃላፊነት የጀመሩ ሲሆን በተለያዩ የመንግስት እና የግል ጤና ሳይንስ ኮሌጆች በመምህርነት አገልግለዋል። በተጨማሪም የዞን እና የክልል የእናቶች እና ህፃናት ጤና ፕሮግራሞች (ICCM/CBNC) ላይ በአስተባባሪነት እና መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት (JSI/L10K) ለስምንት ዓመታት አገልግለዋል። የጤና ሚኒስቴርን ከተቀላቀሉ በኋላ የፈተና አዘጋጅ ቡድን መሪ እና የጤና ባለሙያዎች ብቃት ምዘና እና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር በመሆን የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

በህዝን ጤና ላይ በእናቶችና ህጻናት ጤና፣ የጤና ባለሙያ ብቃት ምዘና እና ቁጥጥር መርሃ ግብሮች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ከአስራ ሶስት አመታት በላይ ልምድ ያካበቱ ሲሆን በፕሮግራም ዘርፎች፣ በጤና ስራ ሃይል እና በተቋማት ልማት ፕሮግራሞች ላይ የበለጠ እንዲማሩ እድል ሰቷቸዋል።

ኢ-ሜይል፡ eden.workneh@moh.gov.et

ስልክ፡

ፋክስ፡