በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የደሴና የኮምቦልቻ ጤና ተቋማት በአሸባሪውና ወራሪው የህውሃት ቡድን አገልግሎት እንዳይሰጡ ሆነው ወድመዋል፡፡
በደሴ ከተማ የሚገኘው የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሸባሪውና ወራሪው የህውሀት ቡድን አገልግሎት እንዳይሰጥ ሆኖ የወደመ ሲሆን ቡድን በተደራጀ መልኩ የህክምና መሳሪያዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ጭኖ ከመውሰዱ ባለፈ የቀሩትንም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አድርጎ ሙሉ በሙሉ አውድሟቸዋል።
ከእነዚህም መካከል በተኝቶ ህክምና፣ በፅኑ ህክምናና በአንስተኛና በከፍተኛ የቀዶ ህክምና ክፍሎች የነበሩ በብዙ ሚሊዮን ብር የተገዙ የትንፋሽ መስጫ /ventilator/ እና አንስቴዥያ ማሽኖች የተወሰዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በመውደማቸው በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል።