በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ተጀመረ 

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር  ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 5 የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስጀምረዋል።


መርኃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።


ጤና ሚኒስቴርና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በዘንድሮው መርሐግብር 12 አቅመ ደካሞችን በአዲስ አበባ እና 5 ቤቶችን በክልሎች የሚገነቡ ሲሆን ይህም የእርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህልን የሚያዳብርና ለመጪው ትውልድም መልካም እሴትን የሚያሸጋግር ታላቅ በጎ ስራ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፡፡


በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች የአቅመ ደካማ ወገኖቻንን ቤት ከማደስ በተጨማሪ የችግል ተከላ መርሃ ግብሮች እየተከናወኑ እንደሆነና በቀጣይም በመላ አገሪቱ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የነጻ ህክምና አገልግት ለመስጠት እንደታቀደ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡


በ2014 ዓ.ም መርሐግብር የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በአዲስ አበባ እና በክልሎች የ22 አቅመ ደካሞችን ቤት ገንብተዉ ማስረከባቸው ይታወሳል።