የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ጤናን ለማሻሻል የሚረዳ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለጤና ሚኒስቴር 31,076,584 ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ,በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ጤናን ለማሻሻል በዩኒሴፍ አመቻችነት የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ባደረገው  የገንዘብ ድጋፍ የህክምና መሳሪያዎች እና ለትራንስፖረት አገልግሎት የሚውሉ ሞተር ሳይክሎችን ለጤና ሚኒስትር አስረክቧል፡፡


የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተደረገውን ድጋፍ አስመልክቶ በርክክብ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት ድጋፉ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ህክምናን ለማሳደግ ከማገዙም በላይ በቤኒሻንጉልና በአፍር ክልል የጨቅላ ህጻናት ህክምናን በመደገፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የተናገሩት ዶክተር ሊያ ታደሰ ለተደረገውም ድጋፍ ለኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) እና ለዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት ምስጋናቸውን በማቅረብ ድጋፉ በክልሎቹ ያለውን አዲስ የተወለዱ ህፃናትን ሞት መቀነስ እና ደህንነታቸውን ማሻሻል እንዲቻል የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል፡፡


የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሶንግሄ ቾ በበኩላቸው ድጋፉን አስመልክተው እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ያለውን የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ህክምና ለመደገፍ በማሰብ የህክምና መሳሪዎችን ድጋፍ ለቤንሻንጉል ጉሙዜ እና አፋር ክልሎች የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ጤናን ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተናግረው ድጋፋም በዩኒሴፍ አስተባባሪነት በኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎበት የቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ 


ዶ/ር ጌንፍራንኮ ሮቲግሊአኖ በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት አዲስ የሚወለዱ የሕፃናት ጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የተደረገው ድጋፍ ትልቅ ጥቅም እንዳላቸው ገልጸው የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ለሚያደረገው ቀጣይ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡