በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ፕሮጀክት ባለፉት ስድስት አመታት ከ58 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት አግኝተዋል።

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ፕሮጀክት በማስተባበር ፓዝፋይንደር ከአሜሪካ እና ከኮሪያ ህዝብና መንግስት በሚደረግለት ድጋፍ ባለፉት ስድስት አመታት በስድስት ክልሎችና በ451 ወረዳዎች ፕሮጀክቶችን ሲሰራ መቆየቱን ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከዩኤስኤአይዲ ትራንስፎርም  ፕኤችሲዩ ጋር በመተባበር በመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልል ጤና ቢሮዎችና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጥራት ያለው የስነ ተዋልዶ፣ የእናቶች፣ የጨቅላ ህፃናት፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች እንዲሁም የስነ ምግብ አገልግሎቶች ተግባራዊ መደረጋቸው ዶ/ር ሊያ ታደሰ አንስተዋል፡፡

በዩኤስኤአይዲ ትራንስፎርም  ፕኤችሲዩ በመጀመሪያ  ደረጃ ጤና ክብካቤ የሚከናወን ተግባራት ከጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር በማናበብና በማሰላሰል የተሰራው በመሆኑ ከጤና ኤክስቴሽን እስከ ሆስፒታል ድርስ የአገልግሎት አሰጣጡ መሻሻል እንዳሳየ ዶ/ር ሊያ ታደሰ  ጠቁመዋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ፕሮጀክት ተግባራዊ በተደረጉበት አመታት አገሪቱ የተለያዩ ፈተናዎችን ያስተናገደች ቢሆንም ችግሩ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ የድንገተኛ ምላሽ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዩኤስኤአይዲ ትራንስፎርም  ፕኤችሲዩ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ባለፉት ስድስት አመታት ከ50 በመቶ በላይ ከፍ ያሉ ሲሆን የጤና መድህን አገልግሎት መሻሻል እንዳሳየም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በደረገባቸው ክልሎች የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት 31 በመቶ አገልግሎቱ መሻሻል ያሳየ ሲሆን በጤና ተቋማት  የሚወልዱ እናቶች ቁጥር 11 በመቶ እንደጨመረ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡

በዩኤስኤአይዲ ትራንስፎርም  ፕኤችሲዩ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ባለፉት ስድስት አመታት ከ1 መቶ12 ሺ በላይ የጤና ባለሙያዎች በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠናዎች እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካና የኮሪያ ህዝብና መንግስት የኢትዮጵያን የጤና ሴክተር ለማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ለማሻሻል እየተደረጉ ያሉ ድጋፍች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ጥሪ አቅርበዋል፡፡    

ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፉት ስድስት እመታት በመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ፕሮጀክት ላይ በአስተባባሪነት ከፍተኛ እስተዋጽኦ ያበረከተዉን  ፓዝፋይንደር እንዲሁም በፕሮጀክቱ የተሳተፉትን ጀ‍ኤስ አይ፣ ኮምፓስ፣ ሀብት አሶሼትስ፣ ማላሪያ ኮንሰርትዬም እና የኢትዮጵያ ምድዋይፎች ማህበርን እመስግነዋል።

በመድረኩ አጋር ድርጅቶቹ  ያከናወኑትን አንኳር ተግባራት በንግግር መልክ ያቀረቡ ሲሆን ቀበሌዎች፣ ወረዳዎች፣  ዞኖችና ክልሎች በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ትራንስፎ ርም ፕእች   ሲዩ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንደነበሩ ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡