የኢትዬጵያ ሕብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት 5 ሚሊዮን ብር እና ከ200 ሺ ብር በላይ የሚገመት አልባሳት ድጋፍ ተደረገ

  • Time to read less than 1 minute
Defense Force

በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባስተላለፉት መልእክት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ህልውና እና እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይህን ታሳቢ በማድረግ ያደረገውን ድጋፍ አመስግነዋል። ይህም ድጋፍ 5 ሚሊዬን ብር እና ከ200 ሺ በላይ የሚገመቱ አንሶላዎች፣ ቢጃማና ነጠላ ጫማዎች መሆኑንም ገልፀዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ምንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ በበኩላቸው የጤናው ዘርፍ በዚህ ፈታኝ ወቅት ለሀገር እያደረገ ያለው አበርክቶ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው አሁንም በገንዘብና በዓይነት በኢትዬጵያ ሕብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት የመጣው ድጋፍ ለመከላከያ ሠራዊት የሚሰጠው አገልግሎት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ በመከላከያ ሰራዊት ስም አመስግነዋል።

የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጽጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው ተቋሙ የህልውና ዘመቻ ከተጀመረ አንስቶ የራሱን አስተዋጾ ሲያደርግ እንደነበር አውስተው አሁንም የመከላከያ አጋርነታችንን ለማሳየት ይህንን ድጋፍ አዘጋጀተናል ።በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።