ወ/ሮ ትግስት ወልደገብርኤል

Tesfaw
የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ወ/ሮ ትግስት ወልደገብርኤል ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ማስተርስ ያላቸው ሲሆን በMOH ውስጥ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። በ2003 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን እንደ ጁኒየር አካውንታንት ሥራ የጀመሩ ሲሆን ለ 2 ዓመታት በዚሁ ስራ ቆይተው በራሱ ቢሮ ውስጥ አጠቃላይ አካውንታንት በመሆን ለ 6 ዓመታት አገልግለዋል። የስራ ዘርፋቸውን ወደ ፐርቼዘር በመለወጥ በዚያው ዞን በግብርና ምርምር ተቋም ውስጥ ለ 2 ዓመታት ሰርተዋል።

ከላይ የተጠቀሱትን ልምዶች አግኝተው በ 2013 አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብቃት ማዕከል (COC) እንደ ከፍተኛ ኦዲተር ከዚያም የፋይናንስ ኃላፊ ተቀላቀሉ። ትምህርታቸውን ወደ MA በማሳደግ እና ልምዶችን በማዳበር በ2015 በማህበራዊ ደህንነት ሚኒስቴር እና በMOWCA ውስጥ የውስጥ ኦዲት ቡድን መሪ ለመሆን በቅተዋል። በ2017 በሴቶች እና ሕፃናት ጉዳዮች ሚኒስቴር የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ካገለገሉ በኋላ ወደ ብሔራዊ የደም ባንክ ተዘዋውረው በተመሳሳይ ቦታ እንደ የውስጥ ኦዲት እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አገልግለዋል።

በአሁኑ ጊዜ የውስጥ ኦዲት ተቋም (IIA) ብሔራዊ ፈተና ላይ የላቀ ውጤት በማስመዝገባቸውና በሌሎች የድርጅት ሥራዎች ስኬታማ በመሆነቸው በ MOH ውስጥ እንደ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኖ ለመስራት በ MOF መስከረም 2019 ተመድበው እየሰሩ ይገኛሉ።

 

ኢ-ሜይል፡tigistmowea@gmail.com

ስልክ፡0115509904

ፋክስ፡0115516396