በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጋምቤላ ክልል የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ተጀመረ 

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

በ2014 በጀት ዓመት በጤና ሚኒስቴር አስተባ ባሪነት ተጠሪ ተቋማትን ባከተተ መንገድ የተለያዩ የክረምት በጎፍቃድ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።


 የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ዛሬ በጋምቤላ ከተማ፣ የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳትን አስጀመሩ። በዚህም የ 5 አቅመ ደካሞች ቤት ሙሉ በሙሉ የሚታደስ ይሆናል።


በክልሉ የአቅመ ደካማ ወገኖችንን ቤት ከማደስ ፕሮግራም ማስጀመር በተጨማሪ  የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ  ሆስፒታል  የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ፣ በክልሉ የሚገነባው ሪጅናል ላብራቶሪ ግንባታ ሒደት፣ እንዲሁም አሻራችን ለትውልዳችን በሚል መሪ መልክት  በጋምቤላ ከተማ ጤና ጣቢያ የችግኝ ተከላ ተካሒዷል። 


 በመርሀ ግብሩም በክልሉ በዝቅተኛ ገቢ ከሚተዳደሩ የአቅመ ደካማ ልጆች ለ400 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ድጋፍ ተደርጓል። 


የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባደረጉት ንግግር  በክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ተደራሽ የሚሆኑት የህብረተስብ ክፍሎች የመክፍል አቅም የሌላቸው አቅመ ደካማ ዜጎቻችን የመደገፍ በሁሉም መስኮች እየተገበረ ይገኛል ብለዋል። 


አያይዘውም በጎነት ለጤናችን በሚል መሪ መልክት የሚካሄደው የክረምት የበጎ ፍቃድ ዘመቻ አቅም ለሌላቸው ዜጎች የነፃ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ በበጎፍቃደኛ ባለሙያዎችና የግል፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የመንግስት ጤና ተቋማትን በማስተባበር ለማካሂድ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ ይህ የመደጋገፍ ተግባር ሁሉም ተባብሮ ሲሰራ ሀገርን ከመገንባት አኳያ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል። 


በፕሮግራሙም በክልሉ ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ1000 በላይ የፍራፍሬ እና የተለያዪ የዛፍ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ብሎም ንፁህ አካባቢና ጤናማነት ትውልድን ለመፍጠር እንዲሁም በስርአተ ምግብ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅኦ  እንዳለው ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። 


ክልሉ የወባ ወረርሽኝ የሚከሰትባቸው አካባቢዎች አንዱ በመሆኑ በቀጣይም  ትኩረት በመሰጠት እንደሚሰራም ገልጸዋል። 


መርኃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ፣ የጤና ሚኒስቴርና፣ የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ የጋምቤላ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ የካቢኔ አባላት፣  የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።


የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ታንኳይ ጆክ የጤና ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማት አመራርና የስራ ሀላፊዎች ከክልሉ ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሚገኙ በመግለጽ በዛሬው ዕለትም በክልሉ ለተካሄዱ የክረምት የበጎ በፍቃድ ስራዎች በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።