በኢንዶኔዢያ ጃካርታ በውሃ፣ በሳኒቴሽን እና በሃይጅን ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከ37 ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ሚኒስትሮች የልምድ ልውውጥ እና ውይይት እያካሄዱ ነው

  • Time to read less than 1 minute
 በውሃ፣ በሳኒቴሽን እና በሃይጅን ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከ37 ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ሚኒስትሮች የልምድ ልውውጥ እና ውይይት

በመድረኩ በዓለም መንግስታት የሚደገፍ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ሲቪክ ማህበራት፣ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች፣ የልማት ባንኮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ውይይቱ በዘላቂ የልማት ግብ 6 ማለትም ዘላቂ የመሰረታዊ ውሃ፣ ሳኒቴሽን እና ሀይጅን አገሌግሎት ለሁሉም ማዳረስ ላይ ያጠነጠነ ነው።

በጃካርታ እየተካሄደ ያለው መድረክ በዋነኝነት በ2030 እ.ኤ.አ የውሃ፣ ሳኒቴሽን እና ሀይጅን አገልግሎቶችን ግብ ለማሳካት ወሳኝ በሆኑት የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ተጨማሪ ኢንቨስትመንት፣ አመራር እና ተጠያቂነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።

በሁለት ቀናት ቆይታው ከውሃ፣ ከሳኒቴሽን እና ከሃይጅን ርዕሰ ጉዳዮች በተጨማሪ የጎንዮሽ ውይይቶች በዘርፉ ሚኒስትሮች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ ኢትዮጵያን ወክለው የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እና የውኃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እየተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ37 ሀገራት የመጡ ከ70 በላይ የዘርፉ ሚኒስትሮችና 250 ልዑካን ተገኝተዋል፡፡

መድረኩ ኢትዮጵያ በውሃ፣ ሳኒቴሽን እና ሃይጅን ስራዎች ልምድ የምታጋራበት እንዲሁም ከሌሎች አገራት ልምድና ተሞክሮ የምትቀስምበት ይሆናል።

‘Building Forward Better for Recovery and Resilience’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡