በሀገራችን ያለውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር የሚያችል አውደ ጥናት ተካሄደ 

  • Time to read less than 1 minute
basic health care financial system

በቅርቡ የታተመው የላንሴት ግሎባል የጤና ኮሚሽን ሪፖርት ላይ በማተኮር "የህብረተሰብ ጤና ክብካቤ ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ሰውን ማስቀደም" በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ፋይናንስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶችን በማካተት አውደ ጥናት አካሄዷል፡፡


በአገራችን በሽታን በመካከልና ጤና ማበልጸግ ፖሊሲን በመቅረጽ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ዘዴን ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝና የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ማሻሻያ ፍኖተ ካርታንም በመዘርጋት ሞዴል ወረዳዎችን ለመፍጠር፣ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሸፋንን ለማሳደግ እና ሁሉንም የጤና ተቋማት ወደ ከፍተኛ አፈጻጸም ለመቀየር በመላ ሀገሪቱ እየተሰራበት እንደሚገኝ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡


እንደ ዶ/ር ሊያ ገለጻ በላፉት አመታት የእናቶችና ሕጻናት ጤና በማሻሻል፣ እንደ ወባ፣ ኤችአይቪ፣ ቲቢ እና ሌሎችም ዋና ዋና ተላላፊ በሽታዎችን በመከላልና በመቆጣጠር እንደዚሁም የክትባት አገልግቶችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ውጤቶችን ለማስመዝገብ እንደተቻለ ገልጸው በቀጣይ ጠንካራ የጤና አገልግሎት ስርዓት እና ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግት ሽፋንን ለማሻሻል የዛሬው መድረክ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል፡፡ 


በጥናቱ ምክረሀሳብ መሰረት መሰረታዊ የጤና እንክብካቤ የፋይናንስ ስርዓትን ለማጠናከር ይቻል ዘንድ ከመንግስት የሚመደበውን የገንዘብ መጠን ማሳደግ ፣ አጋር ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን የፋይናንስ ድጋፎች መጨምር እንደሚገባ ሚኒስትሯ ጠቅሰው ለመሰረታዊ የጤና አገልግሎት የሚመደበውን ገንዘብ በአግባቡ እና በቁጠባ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡


የላንሴት ግሎባል ጤና ኮሚሽን በፋይናንስ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ በገንዘብ ለመደገፍ በማስረጃ የተደገፉ ድርጊቶችን ማዘጋጀት ላይ አተኩሮ መስራቱ በሀገራችን ያለውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር የሚያችል ጥናት አከናውኖ በማሳተሙ ፕሮፌሰር ካራ ሃንሰን እና ቡድናቸውን ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አመስግነዋል፡፡


በአውደ ጥናቱም የለንደን እስኩል ኦፍ ሀይጅን እና ትሮፒካል ሜዲሲን እንዲሁም ላንሴት ግሎባል ሄልዝ ኮሚሽን፣ ፕሮፌሰር ካራ ሃንሰን ለፓናል መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፋይንሲንግ ስርዓትን ለማጠናከር የሚረዱ ጽሁፎችን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡