ዶ/ር ኢሉባቦር ቡኖ

Elubabor Buno
የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ

ዶ/ር ኢሉባቦር ቡኖ ከታህሳስ 2023 ጀምሮ የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ዶ/ር ኢሉባቦር በሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚነት ከመሆናቸው በፊት ከህዳር 2018 ጀምሮ በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታለ በስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡ በሆስታል ቆይታቸው የሆስፒታል አገልግሎት በውጤታማነት የመሩ እና በConsultant Neurosurgeon ከፍተኛ ልምዳቸውን በመጠቀም በህክምናና በስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር ኢሉባቦር ከጥሩነሽ ቤጂንግ በፊት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በNeurosurgery ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ያገለገሉ ሲሆን በዚህም በነበራቸው ልዩ ክህሎትና ቁርጠኝነት በሙያው አንቱታን አትርፈዋል፡፡ በተጨማሪም በአርሲ ዩኒቨርሲቲ አሰላ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል Neurosurgeon እና በቀዶ ህክምና የትምህርት ክፍል በሃላፊነት እንዲሁም የሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት ቺፍ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚህም በፊት በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በጠቅላላ ሀኪምነት ለማህበረሰቡ አስተዋጾ ያደረጉ ሲሆን ከዛም በመቀጠል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአስተማሪነትና የህክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡