ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ሉባ

Dr. Tegene Regassa
የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ

ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ሉባ በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ እና የሀገሪቱ ፓርላማ አባል ናቸው። ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ የማህበራዊ ህክምና እና ጤና አስተዳደር የዶክትሬት ዲግሪ አላቸው። ላለፉት 5 ዓመታት በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።
ለጤና ኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂ፣ ኮቪድ 19ን ጨምሮ ለድንገተኛ አደጋዎች የመረጃ ስርጭት መመሪያዎችን እና ፕሮቶኮሎችን በማዘጋጀት እና እንደ ኤችአይቪ ኤድስ፣ ቲቢ፣ ወባ፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና፣ ክትባት እና የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ላይ ትልቅ የጤና ኮሚዩንኬሽን አመራር አስተዋፅኦ አላቸው። በተጨማሪም የጤና ሚዲያ ፎረም፣ የፌዴራልና የክልል የህዝብ ግንኙነት፣ የጤና ኮሙዩኒኬሽን ኔትዎርክ እና ነጻ የስልክ አገልግሎት ተመስርቶ እንድጠናከር የአመራር ድርሻቸዉን ተወጥተዋል።
በተጨማሪም በምርምር ላይ በንቃት የሚሳተፉ ሲሆን  በአለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ የጥናት ጽሁፎችን አሳትመዋል፡፡