ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን

Hiwot Solomon
በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ ወባና ሌሎች ቬክተር ተላላፊ፣ ቲቢ፣ ስጋ ደዌ እና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ የአይን ጤና፣ የአእምሮ ጤና ትኩረት የሚፈልጉ የትሮፒካል በሽታዎችን በመምራት ላይ ይገኛሉ። በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ፕሮግራም አመራርዝ በርካታ ልምድ አላቸዉ። ቀደም ሲልም በበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ኤች አይ ቪ እና ሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመምራት በዳይሬክተርነት አገልግለዋል።  ሃገር አቀፍ የተለያዩ የጤና ፕሮግራም ስትራቴጂክ ዕቅዶችን፣ መመሪያዎችን፣ የፕሮግራም ግምገማ እና የሃብት ማሰባሰቢያ ሰነድ ማዘጋጀትን የመሳሰሉ  እና የፖሊሲ ሰነድ ዝግጅቶች ላይ ተሳትፈዋል። ለሰባት ዓመታት የወባ መከላከልና መቆጣጠር ሃገር አቀፍ አስተባባሪ  በመሆን በተሳካ ሁኔታ  የመሩ ሲሆን በወቅቱም  የወባ መከላከልና መቆጣጠር መርሃ ግብሩ ከወባ ቁጥጥር ወደ ወባ ማጥፋት ምዕራፍ በማሸጋገር አፍተኛ ድርሻ አላቸዉ።

ዶ/ር ሕይወት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሕብረተሰብ  ከኔዘርላንድስ ማስትሪችት ዩኒቨርሲቲ፣ የ ጤና ዶክተራቸውን ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።