ራዕይ
- ጤናማ አምራችና የበለፀገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ
- ውጤታማ በሆነ መንገድ የጤና ሪፎርሞችንና የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በመተግበር፤ የተናበበና ተገልጋይ ተኮር ለውጥ አምጪ ተግባራትን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመፈጸም የጤና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፡፡
አላማ
- የለውጥ አምጪና የእርስ በዕርስ የስራ ግንኙነት ተግባራት ውጤታማ በማድረግ የስራ አፈጻጸምን ማሻሻል
- የዜጎች ቻርተርን ትግበራን በማጠናከር የዘርፉን የስታንዳርድ ትግበራ አቅምን ለማሻሻል
- የአገልግሎት ማሻሻያ ጥምረትን በመተግበር የፕሮግራሞችን አፈጻጸም ማሻሻል
- የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን፣ የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓትን፣ እንዲሁም የአመራር ተጠያቂነት ስርዓትን በመተግበር የዘርፉን ሀብት አጠቃቀምን ከብክነት መከላከልና የተጠያቂነት ስርዓትን ማጎልበት፡፡
- የተገልጋዮችን ሃሳብና አስተያየት እንዲሁም ቅሬታዎች በተገቢው ምላሽ በመስጠት አገልግሎቶች አሰጣጥ ጥራት ደረጃን ማሻሻል
- የማህበረሰብ አገልግሎት ማሻሻያ ካውንስል አሰራር ስርዓትን ማጠናከር
የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባር
- በጤናው ዘርፍ የሚተገበሩ የሪፎርም ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ፍኖተ ካርታ፣ እንዲሁም ማኑዋሎችን ማዘጋጀትና መተግበር
- የሆስፒታል መልካም አስተዳደር ኢንዴክስ ልኬት ምዘና ማካሄድና መከታተል
- የሆስፒታል መልካም አስተዳደር ኢንዴክስ ልኬት ምዘና ተቋማዊ ማድረግና አፈጻጸሙን መከታተል
- በመጀመሪያ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓትን ትግበራን ማካሄድ
- የጤናው ዘርፍ የለውጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች ማሻሻያ ዕቅድ እንዲታቀድ ማድረግና አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ማድረግ
- ውጤታማነታቸው የተረጋገጡና ለውጥ አምጪ ስትራቴጂዎችን ለጤናው ዘርፍ በሚመች መልኩ በመለወጥ መተግበር
- የጤና ተቋማትን አፈጻጸም የክትትልና ድጋፋ ግምገማ ስርዓቶችን መተግበር
- የተገልጋዮችን አስተያየት መቀበል፣ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መመርመርና ተገቢውን ምላሽ መስጠት፡፡
- የለውጥና መልካም አስተዳደር ፕሮግራሞችና ተግባራትን አቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት
- የክልሎች፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱንና የተጠሪ ተቋማት የሪፎርም ተሳትፎ የሚያሳድጉ ተግባራትን መከወን
- የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ ተቋማዊ ማድረግ
- የአገልግሎት ማሻሻያ ካውንስል ትግበራን መምራት
- ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት መስራት
- የተለያዩ አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ጥምረት ፎረሞችን መከታተልና መደገፍ
የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ኢኒሼቲቭስ
- የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓትን
- የአመራር ተጠያቂነት ስርዓትን
- የመልካም አስተዳደር ኢንዴክስ ምዘና