የክሊኒካል አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

ራዕይ

በሁሉም የጤና ተቋማት ውስጥ ሁሉም ሰው በተቻለ መጠን የተሻለ አገልግሎትና ጤና እንዲኖረው

 

ተልዕኮ

ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን በመፍጠር ጤናንና የጤና አገልግሎቶችን ማሻሻል እና በሁሉም ሆስፒታሎች ላይ የማህበረሰብ እምነትን ማዳበር።

 

ዓላማ

ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በሃይማኖታቸው ፣ ጎሳቸው ፣ ማህበራዊ ደረጃቸው ፣ ዕድሜያቸው እና ጾታቸው ሳይለያዩ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለመፍጠር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሥርዓቶችን ማዘጋጀት።

 

ተነሳሽነት

 

  1. የሆስፒታል አመራር እና አስተዳደርን ማሻሻል
  2. ክሊኒካዊ አመራርን ማሻሻል
  3. የስፔሻሊቲ እና የሰብ-ስፔሻሊቲ አገልግሎቶችን ማስፋፋት
  4. የማገገሚያ ማዕከል አገልግሎቶችን ማጠናከር እና ማስፋፋት
  5. የዲያግኖስቲክ አገልግሎቶችን ማጠናከር እና ማስፋፋት
  6. የሆስፒታል አገልግሎት ሪፎርሞችን ተግባራዊነት መከታተልና መደገፍ
  7. የጤና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻል እና ማስፋፋት

 

ቡድን/የጉዳይ ቡድን/መዋቅር

  • የክልል ሆስፒታል ማሻሻያ ጉዳይ ቡድን (HCT)
  • የፌዴራል ሆስፒታሎች ማሻሻያ ጉዳይ ቡድን (FCT)
  • የልዩ አገልግሎቶች ማሻሻያ ጉዳይ ቡድን (SCT)

 

ሚና እና ኃላፊነቶች

  • የሕክምና አገልግሎቶችን ጥራት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ማዘጋጀት
  • የሕክምና አገልግሎቶችን የበለጠ ደንበኛን ማዕከል ያደረገ ለማድረግ የማሻሻያ ሀሳቦችን ፣ ልምዶችን እና ስርዓቶችን ማዳበር
  • የጤና አገልግሎቱ ከመማር ማስተማርና ከምርምር አገልግሎቶች ጋር የተዋሃደ ስርዓት እንዲኖረው በማድረግ የፌዴራል እና የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል።
  • የአገሪቱን የስፔሻሊቲ ሕክምና አገልግሎቶች ማስፋፉት ፣ ማሻሽልና ማጠናከር።
  • በጤና ተቋማት መካከል የመማርና ማስተማር እና የሀብት መደጋገፍን በመካከላቸው ለማምጣት ያለመ አጋርነት ለመፍጠር ስርዓት መዘርጋት።
  • የጤና ማገገሚያ አገልግሎቶችን ማስተባበር ፣ ማሻሽልና ማጠናከር።
  • በሕክምና አገልግሎቶች መስክ የሚሰሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማስተባበር እና መከታተል
  • የሕክምና አገልግሎቶችን ለማሻሻል ሊያገለግሉ የሚችሉ የተለያዩ ሀብቶችን መሰብሰብ ፣ መምራት እና ማስተባበር።