ጋዜጣዊ መግለጫ

አሁን ላይ በአገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ 19 ክትባት እና ዛሬ በተጀመረው የ2ኛ ዙር የኮቪድ 19 ክትባት  ዘመቻ መርሃ ግብር ዙርያ ከጤና
ሚኒስቴር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ኮቪድ-19 እንደ ዓለም አቀፍ በወረርሽኝ መልክ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ አገራችንን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ማህበራዊ ፣ ኢከኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ሌሎች ተዛማች ችግሮችን እያደረሰ ይገኛል፡፡ አሁንም ወረርሽኙ የማህረሰባችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሁኖ የቀጠለ ሲሆን አገራትም ወረርሽኙን ለመግታትና ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

መረጃዎች እደሚያሳዩት እስከዛሬዋ ቀን  በአጠቃላይ፣  ከ467 ሺ በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ፣ የጽኑ ህሙማን  ቁጥርም ባለፉት አስር ቀናት ከ157 እስከ 233 የደረሰ  ነበሩ፣ እስለዛሬዋ ቀን 7,424 ሰዎች ወገኖቻችን ህወታቸውን አጥተዋል ፣ ባለፈው ሰባት ቀን ብቻ፣ 61 ሰዎች ሞተዋል፡፡

እንዚህ አህዞች የሚያመለክቱን አሁንም ድረስ ኮቪድ 19 በሽታ የዜጊቻንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ እና እንደአገር ያላጠናቀቅነው እና እንቅልፍ የሚነሳን የቤት ስራ እንዳለብን የሚያሳይ ነው፡፡በመሆኑም ሁሌም ቢሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚረዱንን የመከላከያ እርምጃዎች መተግበር ላይ መዘናጋት የለብንም የሚለውን ማሳሳቢያዬን በዚህ ዘጋጣሚ ማስላፍ እፈልጋለሁ!

ሌላው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19ን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ለዉጥ እንደሚያመጡ ትልቅ ግምት የተሰጣቸዉ ክትባቶች በየሀገራቱ ለዜጎች እየተሰጡ ሲሆን በሽታው የሚያደርሰውን አስከፊ ጉዳትና ሞት ለመቀነስ አልፎም ወረርሽኙን ከመቆጣጠር አኳያ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል ተብለው በአለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማታቸው በሳይንሳዊ መንገድ ተፈትሸው የተረጋገጡ ክትባቶች አገራችንን ጨምሮ በዓለም የአገራት እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡


በአገራችንም የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት መስጠት ከተጀመረበት ከመጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቀን ድረስ ከ 10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ክትባት አግኝተዋል፣ ከ 4 ሚሊዮን በላይ ያሉ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ክትባት ወስደዋል፡፡ ከእዚህ ውስጥ 5.5 ሚሊዮን የሚሆነው ሰው በአጭር ግዜ ውስጥ በመጀመሪያ ዙር የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ  የተሰጠ ነው፡፡ በጥቅሉ ከ11 ሚሊዮን በላይ ክትባት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ክትባቶች ሲሰጡ ክትባቶችን በመደበኛ የክትባት አግልግሎት በጤና ጣቢያዎች እና በዘመቻ መልክ የተሰጡ ሲሆን እንደሚታወቀው በአገርአቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት የተካሄደ ሲሆን በዚህም ውጤቶችንና ልምዶችን አግኝተንባቸዋል፡፡  

ለአብነትም ፡- የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በአፍሪካ አሀጉር የመጀመሪያ የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ተሞክሮም ለሌሎች ሀገራትም ጭምር ልምድ ልውውጥ ተደርጓል፡፡ በአጠቃለይ በእዚህ የመጀመርያ ዙር ዘመቻ የሚከተሉትን በርካታ ስኬቶችን እሰመዝግበናል፡፡

  • ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት እንዲያገኙ አድርገናል
  • ህበረተሰቡ ውስጥ የነበሩ የተሳሳቱ መረጃውን ለማስተካከል ትምህርት ተሰጥቷል
  • የአጋር እና ሴክተር መስሪያ ቤቶች ትብብርን ማሳደግ ተችሏል
  • የመከትብ አቅማችን፣ የግባዓት የማሰራጨት አቅማችን ተፍትሾበታል
  • ሀገራችን ባጋጠማት ፖለቲካዊ ጫና ውስጥ ሆና ስራዎችን ማከናወን እንደምትችል አቅማችን መለካት ተችሏል  

እነዚህ እና መሰል ውጤቶችን በመጀመርያ ዙር ዘመቻ የተገኙ ሲሆን አሁንም ያገኘናቸውን ልምዶችና ተሞክሮዎች መነሻ በማድረግ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት አጠናቀን ጀምረናል፡፡ 


ዘመቻው በርካታ ስዎችን በመከተብ ከበሽታው እንዲጠበቁ ማድረግ እና በበሽታው የሚመጣውን ሞት ለመግታት ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን  በዚህም 

  • የህበረተሰብ ቅስቀሳ ስራ በስፋት በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ይስራጫሉ፣ ህብረተሰቡን ለማነቃነቅ ህዝብ በሰፊው የሚቀሰቅሱ ቀስቃሽ ሰዎች ይሰማራሉ እንዲሁም የሚዲያ ዘገባውና ቅስቀሳው በከፍተኛ መንገድ ይጨምራል 
  • ክትባቱን ለህብረተሰቡ በቅርበት ለመስጠት በርካታ ከታቢ ቡድኖች ይዘጋጃሉ ሰዎች በብዛት ወደ ሚገኙበት ቀርበው ክትባቱን ይሰጣሉ
  • የክትባት ስራውን የሚደግፉና የሚከታተሉ በርካተሰ በለሙያዎች ይሰማራሉ
  • በርካታ ክትባት ከማዕከል ወደ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ይሰራጫል 
  • የከፍተኛ አመራሩን ትኩረትና ተሳትፎ ለማሳደግ እና ስራውን እንዲያግዙ ይደረጋል
  • የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ትብብርና ተሳትፎ በከፍተኛው ይጨምራል

በዚህ የሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ  የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ  20 ሚሊዮን በላይ ክትባት ተዘጋጅቶ ለሁሉም ክልል ተሰራጭቷል፡፡ ለዚህ ዘመቻም Pfizer, J and J እና sinopharm ክትባቶች በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅተው ለክልሎች ተሰራጭተዋል ፡፡


ክትባቱ ከእዚህ ቀደም በጤና ተቋማትና በዘመቻ መልክ መስጠታችን ይታወቀል፡፡ ይህኛው ዘመቻ በጤና ተቋማት እና በጊዚያዊ በሚቋቋሙ  የክትባት መስጫ ጣቢያዎች  የካቲት 7 ፣ 2014 ጀምሮ የሚስጥ ይሆናል፡፡ ግዚያዊ  የክትባት መስጫ ጣቢያዎች የሚቋቋሙት ሰው በሚበዛበቸው ቦታዎች ተመርጦ ነው፡፡ ለእዚህም ቦታውን የሚጠቁም እና የሚቀሰቅሱ ሰውች ይኖራሉ፡፡


በእዚህ ዘመቻ እድሚያቸው 12 አመት እና ከእዚያ በላይ የሆናቸው ከእዚህ በፊት የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ያልወሰዱ ፣ እድሚያቸው 12 አመት እና ከእዚያ በላይ የሆናቸው ከእዚህ በፊት የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት 1ኛ ዶዝ ወስደው ሁለተኛውን ዶዝ ለመውስድ ግዚያቸው የደረሰ ሰዎች  ፣ እድሚያቸው 12 አመት እና ከእዚያ በላይ የሆናቸው  ከእዚህ በፊት የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ወሰደው አጠናቀው (ሙሉ ለሙሉ ውስደው) ስድስት ወር የሞላቸው  ሰውች Booster dose የሚሰጣቸው ይሆናል ፡፡


የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታትና በሸታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የምናደረገውን ርብርብ ከማገዝ ባለፈ የክትባት ሽፋናችን ሲያድግ  ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አሉት ለምሳሌ አለም አቀፍ ስብሰባዎችን ሀገራችን እንድስታስተናግድ የበሽታውን ስጋት ለመቀነስ እና ቱሪዝም እንዲስፋፋ እና ኢኮኖሚው እንዲያገግም እና እንዲነቃቃ አንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ አንቅሰቀሴዎች ላይ አውንታዊ  ውጤቶችን ያስገኛል፡፡


በመጨረሻም የኮቪድ 19 ክትባት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እና በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችለውን ሞት እና ፀኑ ህመምን ለመቀነስ የሚያግዝ በመሆኑ በአገር አቀፍ ደረጃ በሁለተኛ ዙር  መከተብ ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በጤና ተቋትና በጊዚያዊ የክትባት ጣቢያዎች እንዲከተቡ እያሣሰብኩ አስካሁን ባደረግነዉ ጥረት በክትባት አቅርቦት፣ በስርጨት፣ ክትባቱን በመስጠት፣ ተገቢዉን መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ በኩል ሀሃሳብና ድጋፍ በመስጠት ለተሳተፉችሁ ሁሉ ምስጋናየን እያቀረብኩ አሁንም ኮቪድ-19 ኝንየመከላከል ስራ ለአፍታም ቢሆን ጊዜ የማይሰጠው እና ለጥቂት ተቋማት የማይተው በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት : መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ ዳግም ትኩረት ለኮቪድ- 19 ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ላይ እንድናደርግ መልክቴን እና ጥርዬን ከአደራ ጭምር ለማስተላለፍ እወዳለሁ!
    
አመሰግናለሁ!

ጤና ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያ
ግንቦት.2013 ዓ.ም