የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት

የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የስራ ሂደት የጤናዉን ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን፤ ተደራሽነትን እና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል፤ አገር በቀልና አዳዲስ ፈጠራ የታከለበት(innovative) በሆኑ ቴክኖሎጂዎች እየታገዘ የጤና አገልግሎትን መተግበር፤ መረጃን በወቅቱ፣በጥራት ለመሰብሰብ፣ ለመጠቀም እና ለማስተላለፍ የሚያስችል የጤና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ተግባራዊ ለማድረግ  እየሰራ ይገኛል፡፡
የሥራ ሂደቱ እንደ አጠቃላይ ከሚተግብራቸዉ ግቦች መካከል ዋናዎቹ እንደ ወጪ ቆጣቢ፣ አገር በቀል እና በፈጠራ ላይ የተመሰረቱ የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎችን በመቀመር ከአገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ጥራት እና ፍትሃዊነትን ወደ ላቀ ሁኔታ ማሻገር ነዉ፡፡ 
በጤናዉ ዘርፍ የተያዙ የትራንሰፎርሜሽን አጀንዳዎችን  ለማሳካት እና የዉስጥ እና የዉጭ ተገልጋዮች አገልግሎት  ጥራትና  ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ጥረት በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ የጤና ስርዓት ለማስቻል የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡-

የዳይሬክቶሬቱ ዋና ተግባራት

 

  • በሁሉም ጤና ተቋማት ላይ ደረጃዉን የጠበቀ ኢኮቴ መሰረተልማት ያስፋፋል፤ ያጠናክራል፤ ያስተዳድራል፡፡
  • በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የጤና መረጃ ለመሰብሰብና ለውሳኔ ሰጭነት በሚያመች መልኩ ማቅረብ የሚያስችሉ ኤልክትሮኒክ የመረጃ ስርዓቶችን ይተገብራል፤
  • በጤና ተቋማት ያለውን የባለሙያ ክፍተት ለመሙላት እና የአግልግሎት ተደራሽነትን የሚያገለግሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ያስፋፋል፤
  • በህክምና የትምህርት ተቋማት ላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማዘመን አስፈላጊውን ቴክኒካል ድጋፍ ያደርጋል፤
  • የመስሪያ ቤቱን የአሰራር ስርዓት የሚያቀላጥፉ ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ይተገብራል
  • የጤና መረጃ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መረጃዎችን ያጠናቅራል፤ ያቀርባል፡፡
  • በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚተገበሩና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በስራ ላይ  የሚውሉ ሲስተሞችና ቴክኖሎጂዎች ላይ የአጠቃቀም ስልጠናዎችን ይሰጣል፤ ትግበራዎች ላይ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም በክልሎችና በተቋማት የሚገኙ የጤና ኢኮቴ ባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ያመቻቻል፤ ይሰጣል፡፡
  • በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚተገበሩ ኤሌክትሮኒክ ሲስተሞችና የኢኮቴ መሰረተልማት ለመተግበር፣ ለማስተዳደር እና ወጥ የሆነ የአሰራር ሂደት አጋዥ የሆኑ የኢኮቴ ፖሊሲዎች፤ ስትራቴጂክ ዶክመንቶች፣ የኢኮቴ ስታንዳርድ ዶክመንቶች፤ ፕሮሲጀሮች እና ስራዎችን የሚያቀላጥፉ አሰራሮችን ያወጣል ይተገብራል፡፡
  • የኢኮቴ መሰረተልማቶች አገልግሎት እንዳይቆራረጡ ያስተዳድራል፤ ጥገና ያካሂዳል፣የማስፋፋት ስራዎችን ይሰራል፣
  • የጤናውን ሴክተር የአሰራር ስርዓት ለማዘመን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ያለማል፤ ያስተዋውቃል፤ ያላምዳል፡፡
  • የሚኒስቴር መስሪያቤቱን ያቀዳቸውን የጤና እርምጃዎች/Initiative/ በኢኮቴ ለመደገፍና ለማሳካት በአገሪቱ ውስጥ ካሉ በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር በጋራ ይሰራል፤ የልምድ ልውውጥ ያደርጋል፡፡
  • ከተጋልጋዮች የሚቀርቡ የኢኮቴ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ የመረጃ ሥርዓቶችን ማበልጸግ/ማላመድ እና መተግበር 
  • አዳዲስ የጤና ኢንፎርሜሽን ሲስተሞችን መለየት እና ማስተዋወቅ፤
  • በተተገበሩ የመረጃ ሥርዓቶች ላይ እና በተለያዩ ተቋማት ለሚሰሩ የአይቲ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት