በአሜሪካ መንግስት 453,600 ዶዝ ጆንሰን ጆንሰን ኮቪድ19 ክትባቶች ለኢትዮጵያ ድጋፍ ተደረገ 

  • Time to read less than 1 minute
donation


ከአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል 453,600 ዶዝ ጆንሰን ጆንሰን ኮቪድ19 ክትባቶች ለኢትዮጵያ ድጋፍ ተደረገ ፡፡


በርክክቡ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሐረላ አብዱላሒ ባደረጉት ንግግር ከአሜሪካ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ክትባት ለአራተኛ ዙር እንደሆነ እና በዛሬው እለትም 453,600 ዶዝ ጆንሰን ጆንሰን ኮቪድ19 ክትባቶችን መረከባቸውን እንዲሁም በቀጣይ ተጨማሪ 504 ሺ ክትባቶች እንደሚገቡ ይፋ አድርገውዋል፡፡


አያይዘውም ወ/ሮ ሰሐረላ አብዱላሂ  ከሰኔ 2021 ጀምሮ እስካሁን ለኢትዮጵያ ከ2.5 በላይ ሚሊዮን ዶዝ በላይ ጆንሰን ጆንሰን ክትባቶች ድጋፍ መደረጉን በመጥቀስ አሁን ካለው ድጋፍ በተጨማሪ  ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ኤጀንሲዎች ጋር ለብዙ ዓመታት አጋር  በመሆን ለሚሰራው  ስራ ለአሜሪካ መንግስትና ህዝብ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ሁሉ ያላቸውን ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።


በርክክቡ ወቅትም የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሐረላ አብዱላሒ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ፤ ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶችም የጃልሜዳ ጤና ጣቢያ በኮቪድ -19 ክትባት ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በተመለከተ ጉብኝት አድርገዋል።