የስርዓተ ምግብ ትግበራን ለማጠናከር የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

በሰቆጣ ቃልኪዳን የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት በማጋራት በአፍሪካ ደረጃ መቀንጨርን ለማስቀረት፣ የሰው ሀብትን ለማሳደግ፣ እና በዘርፉ እድገትን ለማፋጠን አላማ አድርጎ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአፍሪካ ልማት ባንክ ትብብር የተባበሩት መንግስታት አጠቃላይ ጉባኤ እየተካሄደ ባለበት በአሜርካ ኒዉዮርክ ከተማ የተዘጋጀ የጎንዮሽ መድረክ ነው።


በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያ የመቀንጨር ምጣኔን ከመቀነስ አኳያ እየሰራች ያለውን ዘርፍ ብዙ ትብብርና ምላሽ አጠቃላይ ልምድና በሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት የተገኙ መልካም ተሞክሮ በኢፌድሪ  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ቀርበዋል።


በመድረኩ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዘዳንት፣ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮችና አጋር አካላት  የተገኙ ሲሆን ለስርዓተ ምግብ እና የተቀናጀ ዘርፈ ብዙ የስርዓተ ምግብ ምላሽ አስፈላጊውን ሃብት በመመደብና ትኩረት በመስጠት ከአፍሪካ ከፍተኛ የጤና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኘውን መቀንጨርን ለማጥፋት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።