የጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

መግቢያ

የጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በፌደራል መንግስት ስር የሚገኙ የጤና እና ጤና ነክ ተቋማትን ለመቆጣጠርና የክልሉን ጤና ተቆጣጣሪ አካላት ለመደገፍ የተቋቋመ ዳይሬክቶሬት ነው። ዳይሬክቶሬቱ ሁለት የጉዳይ ቡድኖች አሉት ፤ እነዚህም የጤና ተቋማት ተቆጣጣሪ ጉዳይ ቡድንና የጤና ነክ ተቋማት ተቆጣጣሪ የጉዳይ ቡድን ናቸው።

ራዕይ

ደህንነቱ የተጠበቀና ጥራት ያለው የጤና እና ጤና ነክ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ማድረስ

ተልዕኮ

ለጤና ተቋማት ፈቃድ ከመስጠት በፊት በሚደረግ ቅድመ ፈቃድ ምርመራ ፣ ተገቢ ፈቃድ አሰጣጥ፣ እና ድህረ ፈቃድ ምርመራን በመቀጠል፤ እና የጤና ነክ ተቋማት ንፅህና እና የአካባቢ ጤና ፍተሻ በማድረግ ፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ ፣ ትብብርና ወቅታዊ የቁጥጥር መረጃ በመስጠት የጤና እና ጤና ነክ አገልግሎቶችን ደህንነትና ጥራት በማረጋገጥ ህዝብን መጠበቅ።

ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

በፌዴራል መንግሥት ሥር ያሉ የጤና ተቋማትን መቆጣጠር (ቅድመ ፈቃድ ምርመራ ፣ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት እና ማደስ ፣ ድህረ ፈቃድ ምርመራ ፣ የተለዩ ክፍተቶችን እርማት መከታተልና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰድ)

በፌዴራል መንግሥት ስር ያሉ የጤና ነክ ተቋማት  (ዩኒቨርሲቲ ፣ እስር ቤት ፣ የስደተኞች ካምፕ ፣ ከአራት-ኮከብ በላይ ያሉ ሆቴሎች ፣ በአለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ ያሉ የምግብ እና የመጠጥ ተቋማት) ንፅህና እና አካባቢያዊ ጤናን መቆጣጠርና የተለዩ ክፍተቶችን እርማት መከታተልና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰድ

ከኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የብሔራዊ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ስታንዳርዶችን ምስረታና ክለሳ ማገዝ

የብሔራዊ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት ስታንዳርዶች መተግበርን ማረጋገጥ

የዳታቤዝ ስርዓትን (ማስተር ፋሲሊቲ ምዝገባን) በመጠቀም የብሔራዊ ጤና ተቋማትን መረጃ መመዝገብና ሙሉ የብሔራዊ መረጃን መጠቀም

በብሔራዊ ስታንዳርዶች መሠረት ብሔራዊ የጤና ተቋማትን ግምገማ ማካሄድ ፣ የጤና ተቋማትን (አረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ) በሚል መሰየምና እንደ አስፈላጊነቱ እርምጃዎችን መውሰድ

ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት የአቅም ግንባታ እና የስልጠና ፣ ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ

ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ስም - በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማስተላለፍ ማስተር ፋሲሊቲ ምዝገባን (MFR) ማጠናከር