የድንገተኛና ጽኑ ህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

ራዕይ

ለጤናማ ፣ የበለፀጉ እና አምራች ኢትዮጵያውያን የድንገተኛ የጤና አገልግሎት ስርዓትን ማላቅ።

 

ተልዕኮ

በአጣዳፊ ህመም የታመሙ እና በድንገተኛ አደጋ የተጎዱን እንክብካቤ የሚያሻሽል እና ለየተባበረ የጤና አገልግሎት (UHC) እውንነት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ጠንካራና የተባበረ ስርዓትን በሁሉም ደረጃዎች  በመገንባት ፍትሃዊ ፣ የተቀናጀ፣ ያልዘገየና ጥራት ያለው የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህክምና አገልግሎት መስጠት።

በሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል (MSDG) ስር የሚገኘው ለድንገተኛ ጽኑ ህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት (EICCD) ፣ በአጣዳፊ ህመም ለታመሙና በድንገተኛ አደጋ ለተጎዱ ያልዘገየ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ከቅድመ ሆስፒታል አገልግሎትና መጓጓዣ ፣ በሆስፒታል አገልግሎት (የድንገተኛ ክፍል እና አይሲዩ) እንዲሁም የሪፈራል ስርዓትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ይቆጣጠራል።  ከአስቸኳይ አገልግሎት ስርዓት በተጨማሪ EICCD ለአደጋዎች ዝግጁነት እና ክሊኒካዊ ምላሽ ኃላፊነት አለበት።

በድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህመሞች የሚከሰቱ ሞቶችና የአካል ጉዳተኝነቶችን ለመቀነስ በማሰብ ዳይሬክቶሬቱ ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ይሠራል።

  • በድንገተኛና ጽኑ ህክምና አገልግሎት (EICC) ስርዓት ውስጥ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማሻሻል
  • ተነሳሽነትና ብቃት ያለው የEICC የሰው ኃይልን ማዳበር
  • በተቋሙ ላይ የተመሠረተ የEICC አገልግሎትን ወደ ስታንዳርድ ደረጃ ማሻሻል
  • በድንገተኛና ጽኑ ህክምና አገልግሎት ስርዓት ውስጥ የድንገተኛ አገልግሎት መረጃ ጥራትና አያያዝን ማሻሻል
  • ለ EICC አስተዳደርን እና አመራርን ማሳደግ
  • አጋርነትን እና ትብብርን ማጠናከር
  • የቅድመ-ተቋም እና የድንገተኛ ጊዜ ሪፈራል ስርዓትን ማሻሻል
  • ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታካሚዎች የማስተናገድ አቅምና የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ስርዓትን ማጠንከር
  • ዘላቂ የ EICC ፋይናንስን ማሻሻል
  • የ EICC መድኃኒቶችን ፣ የህክምና አቅርቦቶችንና መሣሪያዎችን ተገኝነት ማሻሻል

 

የጉዳይ ቡድኖች

  • የቅድመ-ተቋም ጉዳይ ቡድን
  • የፋሲሊቲ ድንገተኛ ጉዳይ ቡድን
  • የጽኑ ህክምና ጉዳይ ቡድን
  • የሪፈራል የጉዳይ ቡድን

 

ተነሳሽነት /ፕሮግራሞች

  • የዋና ዋና ከተሞች የድንገተኛ እና የጽኑ ህክምና ማሻሻያ ፕሮግራም (MECIP)
  • የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች የኮቪድ 19 ቅድመ ሆስፒታል ጥናት
  • የጽኑ ህክምና ማሻሻያ ፕሮግራም
  • የአደጋ አገልግሎት ስርዓት መሻሻል
  • የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ