የጤና አገልግሎት ጥራት ዳይሬክቶሬት

Quality health service

ራዕይ

ጤናማ ፣ አምራች እና የበለፀገ ማህበረሰብ ማየት

 

ተልዕኮ

ስልታዊ ዕቅድ በማቀድ እንዲሁም ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል እና በመቆጣጠር የኢትዮጵያውያንን ጤና እና ደህንነት ማሳደግ

 

የዳይሬክቶሬቱ ዋና ተግባራት

  1. የዳይሬክቶሬቱን ስትራቴጂካዊ እና ዓመታዊ ዕቅዶች ማዘጋጀት ፣ መተግበር እና መከታተል
  2. የሆስፒታል ማሻሻያ ትግበራ መመሪያዎችን በመደበኛነት ማዘጋጀት፤ ወቅታዊ ግምገማ ፣ ማስተዋወቂያ እና የአሠልጣኞች ሥልጠናን ማስተባበር
  3. በተቋሙ ውስጥ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት አቅርቦትን መደገፍ እና መቆጣጠር
  4. ለተመረጡ የሕክምና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ ስታንዳርዶችን ፣ መመሪያዎችንና ፕሮቶኮሎችን ማዳበር ፤ የሁሉንም የመንግስት የሕክምና ተቋማት ጥራት ለማሻሻል የሕክምና አገልግሎቶችን ማመልከቻዎች መደገፍ እንዲሁም የክሊኒካል ኦዲቶችን መጠናከር መቆጣጠርና መደገፍ።
  5. የሕክምና አገልግሎቶች ከፍተኛ ጥራት እና ደህንነት እንዲኖራቸው  ምርምር በማድረግ ክፍተቶችን መለየትና ኦዲት ማድረግ እንዲሁም የማሻሻያ ስትራቴጂዎችን ማውጣታ
  6. ከአገልግሎት አቅራቢዎች የተሰበሰቡ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾችን በመጠቀም የአገልግሎቶችን ጥራት የሚያሻሽሉ ስልቶችን ማውጣት
  7. ምርጥ ልምዶችን የማጠናቀር እና የማሰራጨት ሂደትን ማዳበርና መቆጣጠር።
  8. በሕክምና አገልግሎቶች አቅራቦት ወቅት የሕክምና ስህተቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል ስርዓት መዘርጋት ፤ አተገባበሩንም መከታተል።
  9. የጤና ባለሙያዎች በባለሙያ ሥነምግባር መሠረት አገልግሎቶችን እንዲሰጡ እና አርአያ የሚሆኑ ባለሙያዎችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ፤ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች በተቋማት ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችለውን ሥርዓት መደገፍና መከታተል
  10. የጤና አገልግሎት መቋረጥ በሚከሰትበት ጊዜ የአቤቱታ አያያዝ ስርዓትን ማቋቋምና መከታተል እንዲሁም ምላሽ መሰጠት።
  11. በተቋማት ሂደት በቀጥታ በመሳተፍና ለተቋማት አጠቃላይ ለውጥ አስተዋፅኦ በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በተቋማት ሂደቶች ላይ ሙሉ ግንዛቤ ያለው የአገልግሎት ተጠቃሚ ማህበረሰብ የመፍጠር ሥርዓትን መደገፍ እንዲሁም መከታተል።
  12. የሕክምና አገልግሎት የጥራት ደረጃዎችን ማዘጋጀት፤ ክፍተቶችን መለየትና የማሻሻያ ፕሮግራሞችን መፈፀምና መቆጣጠር
  13. ከጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሌሎች የአፈጻጸም ማዕቀፎች ጥራት መጠበቅ
  14. ከክልል ፣ ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተቋማት ውስጥ የተቀናጀ የድጋፍ ቁጥጥር ማካሄድ ፤
  15. ጥሩ አፈፃፀም ያላቸውን የጤና ተቋማት በእውቅና አሰጣጥ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ መደገፍ።
  16. የሕክምና አገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል የ ሜንቶርሺፕ እንቅስቃሴዎችን መተግበር
  17. የተለያዩ የጥራት ማሻሻያ ሞዴሎችን ፣ ስትራቴጂዎችን እና መርሆዎችን ተግባራዊና ተቋማዊ ማድረግ።
  18. የጤና አደጋ ምንጮችን መለየት ፣ የድርጊት አቅጣጫዎችን መዘርጋት
  19. የጥራት ባህል ትግበራን ተቋማዊ ማድረግና መደገፍ።
  20. የሆስፒታል አስተዳደር አቅምን መደገፍና መቆጣጠር፣ ሆስፒታሎች ዘመናዊ እና ሙያዊ አስተዳደር እንዲኖራቸው ማስቻል፣ የቦርድ አቅምን እና የፋይናንሻል ለውጥን መደገፍ።
  21. ብሔራዊ የጥራት ምርምር ስብሰባዎችን እና ሥልጠናዎችን ማስተባበር።

 

የብሔራዊ የጥራት ጤና አገልግሎት ስትራቴጂ

የ HSTP Iን መጀመር ተከትሎ የብሔራዊ የጥራት ስትራቴጂ I(NQS) (2016-2020) በ HSTP ውስጥ የተገለጸውን ዓላማ እውን ለማድረግ ተዘጋጀ። NQS I አምስት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የጤና መስኮች እና አራት ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች አስቀምጧል። ይህም አገሪቱ ሀብትን እንድትጠቀም ፣ አስፈላጊውን የጥራት አወቃቀር በየደረጃው እንድትመሠርት እና በጥራት ጥበቃ ላይ የባለሙያዎች ስብስን እንድትፈጥር ረድቷታል። ነገር ግን ባለፉት አምስት ዓመታት የጤና አገልግሎት ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ፍላጎት ታድሷል። በታካሚ ደህንነት እና ጥራት ላይ አዲስ ጣልቃ ገብነቶችና ፅንሰ -ሀሳቦች የተመዘኑ ሲሆን ሰነዶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጋርተዋል።

በዚህ በመመስረት MOH የ NQS I አፈፃፀምን በመገምገም፣ በተገኙት ውጤቶች ላይ በመገንባትና ከስህተት በመማር NQS II (2021-2025)ን በ ‹HSTPII› ውስጥ በተገለፀው መሠረት ለሀገሪቱ አውድ የተስማሙ ፅንሰ-ሀሳቦችንና ጣልቃ-ገብነቶችን በሚያካትት መልኩ መሰረተ።

የአሁኑ ስትራቴጂ ዋና ግብ የሚከተሉትን አምስት ዓላማዎችን እውን በማድረግ የጤና ውጤትን እና በስርዓቱ መተማመንን ማሻሻል ነው:

በማስረጃ ላይ የተመሠረተ አስፈላጊ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ማሻሻል ፣ የተሻሻለ ሰዎችን ማዕከል ያደረገ አገልግሎት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅልጥፍናን ማሻሻል፣ እና በማይቋረጥ ትምህርትና መሻሻል የጥራት ባህልን መፍጠር። ለሁሉም ዓላማዎች፣ ዋና ዋና ተግባራትና ግቦች ተዘጋጅተዋል።

 

ዋና ተነሳሽነት

  1. የእናቶችና ህፃናት ጤና የጥራት አገልግሎት ተነሳሽነት
  2. ደህንነቱ በተጠበቀ የቀዶ ጥገና ሕይወትን ማዳን (SaLTS) ተነሳሽነት