የጤና ሚኒስቴር ከቻይና መንግስት 10 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ተረከበ።

  • Time to read less than 1 minute
from the Chinese

የቻይና መንግስት ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ቃል ገብቶት ከነበረው የ20 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ውስጥ 10 ሚሊዮኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ዛኦ ዚያን እጅ በዛሬው እለት  ተረክበዋል፡፡ 


በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የቻይና መንግስት የኮቪድ 19 በሽታን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እያደረገው ስላለው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል። ለኢትዮጵያ ድጋፍ ከተደረገው 10 ሚሊዮን ውስጥ 5 ሚሊየን የሚሆነው በቻይና መንግስት ቀዳማዊት እመቤት የተበረከተ ሲሆን በአቻቸው የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ስም ለጤና ሚኒስቴር የደረሰ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ሊያ ክትባቱም በዋነኝነት ተደራሽ የሚያደርገው ለእናቶች እና ለወጣቶች መሆኑንም አክለው ተናግረዋል፡፡ 


በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛኢ ዚያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ቀደም ሲል 4 ሚሊየን ዶዝ ክትባት የቻይና መንግስት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረው 10 ሚሊዮኑ በዛሬው ዕለት ማስረከባቸውን እንዲሁም የኢትዮጵያና የቻይና መንግስት ወዳጅነት ረዥም አመት ያስቆጠረ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡